bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
1 Corinthians 2
1 Corinthians 2
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 3 →
1
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔም ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በማባበልና ነገርን በማራቀቅ የእግዚአብሔርን ትምህርት ላስተምራችሁ የመጣሁ አይደለም።
2
ከተሰቀለው ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር በእናንተ ዘንድ ሌላ ነገር እሰማለሁ ብዬ አልጠረጠርሁም ነበር።
3
እኔም በድካምና በፍርሀት፥ በብዙ መንቀጥቀጥም መጣሁ።
4
ቃሌም፥ ትምህርቴም መንፈስንና ኀይልን በመግለጥ ነበር እንጂ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።
5
ማመናችሁ በእግዚአብሔር ኀይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን።
6
ለዐዋቆች ጥበብን እንነግራቸዋለን፤ ነገር ግን የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላቸውን የዚህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይደለም።
7
ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔር ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።
8
የዚህ ዓለም ሹሞችም አላወቁትም፤ ይህንስ ቢያውቁ ኑሮ የክብር ባለቤትን ባልሰቀሉትም ነበር።
9
ነገር ግን መጽሐፍ፥ “ዐይን ያላየው፥ ጆሮም ያልሰማው፥ በሰውም ልቡና ያልታሰበ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ነው።” ብሎ የለምን?
10
ለእኛም እግዚአብሔር በመንፈሱ ገለጠልን፤ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምሥጢሩን ያውቃልና።
11
በሰው ልቡና ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? በእርሱ ያለችው ነፍሱ ናት እንጂ፤ እንዲሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር የእግዚአብሔርን አሳብ የሚያውቅ የለም።
12
እኛ የዚህን ዓለም መንፈስ የተቀበልን አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሚሆነውን መንፈስ ተቀበልን።
13
ይህም ትምህርታችን ከሰው የተገኘ ትምህርት አይደለም፤ የአነጋገር ጥበብም አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ የገለጸው ትምህርት ነው እንጂ፤ መንፈሳዊ ጥበብም ከመንፈስ ቅዱስ የሚሆነውን መርምረው ለሚያውቁ ለመንፈሳውያን ነው።
14
ለሥጋዊ ሰው ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ይመስለዋልና፥ አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቅ አይችልም።
15
መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል፤ እርሱን ግን የሚመረምረው የለም።
16
የእግዚአብሔርን አሳብ ማን ያውቃል? መካሩስ ማን ነው? እኛ ግን ክርስቶስ የሚገልጠው ዕውቀት አለን።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16