bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
2 Corinthians 2
2 Corinthians 2
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 3 →
1
እንግዲህ እያዘንሁ ወደ እናንተ እንዳልመጣ በልቤ ይህን ወሰንሁ።
2
እኔ ካሳዘንኋችሁማ እኔ ካሳዘንሁት በቀር ማን ደስ ያሰኘኛል?
3
የእኔ ደስታ የሁላችሁ እንደ ሆነ በሁላችሁ አምኛለሁና በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ ከሚገባቸው ኀዘን እንዳያገኘኝ ይህን ጻፍሁላችሁ።
4
ከብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት የተነሣ በብዙ እንባ ይህን ጽፌላችኋለሁ፤ ነገር ግን እጅግ እንደምወዳችሁ እንድታውቁ ነው እንጂ እንድታዝኑ አይደለም።
5
ማንም ያሳዘነኝ ቢሆን፥ እኔን ብቻ ያሳዘነ አይደለም። ከእናንተ አንድ ሳይቀር ሁላችሁንም አሳዘነ እንጂ፤ አሁንም ሥርዐት አላጸናባችሁም።
6
እንደዚህ ላለው ሰው ከእናንተ ከብዙዎች ያገኘችው ይህች ተግሣጽ ትበቃዋለች።
7
ደግሞም እንዲህ ያለው ሰው ከኀዘን ብዛት የተነሣ እንዳይዋጥ ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባል።
8
ስለዚህም ከእርሱ ጋር ፍቅርን እንድታጸኑ እማልዳችኋለሁ።
9
ስለዚህም በሁሉ ትታዘዙኝ እንደ ሆነ፥ ፈቃዳችሁን ዐውቅ ዘንድ ጻፍሁላችሁ።
10
ይቅር የምትሉት ቢኖር፥ እኔም ከእናንተ ጋር ይቅር እለዋለሁ፤ እኔም ይቅር ያልሁትን በክርስቶስ ፊት ስለ እናንተ ይቅር ብያለሁ።
11
ሰይጣን እንዳያታልለን አሳቡን የምንስተው አይደለምና።
12
ለክርስቶስም ወንጌል ጢሮአዳ በደረስሁ ጊዜ በእግዚአብሔር በሩ ተከፈተልኝ።
13
ወንድሜን ቲቶን ስላላገኘሁት ለሰውነቴ ዕረፍት አላገኘሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ ተለይች ወደ መቄዶንያ ሄድሁ።
14
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ድል በመንሣቱ የሚጠብቀን፥ በየሀገሩም ሁሉ የዕውቀቱን መዓዛ በእኛ የሚገልጥ እግዚአብሔር ይመስገን።
15
በሚድኑትና በሚጠፉት ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ እኛ ነንና።
16
የሞት መዓዛ የሚገባቸው ለሞት፥ የሕይወት መዓዛ የሚገባቸውም ለሕይወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚገባው ማነው?
17
የእግዚአብሔርን ቃል በሌላ ቀላቅለው እንደሚሸቅጡ እንደ ብዙዎች አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላከ በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ እንናገራለን።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13