bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Deuteronomy 2
Deuteronomy 2
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 3 →
1
“እግዚአብሔርም እንዳለኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።
2
እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦
3
‘ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል፤ ተመልሳችሁ ወደ መስዕ ሂዱ።’
4
ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ሀገር ታልፋላችሁ፤ እነርሱ ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ።
5
የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።
6
ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገንዘብ በመለኪያ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ።
7
አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ ይህን ታላቅና የሚያስፈራ ምድረ በዳ እንዴት እንደ ዞርኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፤ ከተናገርኸው ሁሉ አንዳችም አላሳጣህም።
8
በሴይርም ከተቀመጡት ከወንድሞቻችን ከዔሳው ልጆች በዓረባ መንገድ ከኤሎንና ከጋስዮን-ጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን።
9
“እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው።
10
እንደ ዔናቃውያን ታላቅና ብዙ ሕዝብ ኀያላንም የሆኑ ኦሚናውያን አስቀድሞ በዚያ ይቀመጡ ነበር።
11
እነርሱም ደግሞ እንደ ዔናቃውያን ራፋይም ተብለው ይታወቁ ነበር፤ ሞዓባውያን ግን “ኦሚን” ብለው ይጠሩአቸው ነበር።
12
ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ተቀምጠው ነበር፤ የዔሳው ልጆች ግን መቱአቸው፤ ከፊታቸውም አጠፉአቸው፤ እግዚአብሔርም በሰጠው በርስቱ ምድር እስራኤል እንዳደረገ፥ በስፍራቸው ተቀመጡ።
13
አሁንም ‘ተነሡና ተጓዙ፤ የዛሬድንም ፈፋ ተሻገሩ፤’ የዛሬድንም ፈፋ ተሻገርን።
14
የዛሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለባቸው ተዋጊዎች የሆኑ የዚያች ትውልድ ሰዎች ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።
15
ከሰፈርም መካከል ተለይተው እስኪጠፉ ድረስ የእግዚአብሔር እጅ በላያቸው ነበረ።
16
“እንዲህም ሆነ፤ ተዋጊዎቹ ከጠፉ፥ ከሕዝቡም መካከል ከሞቱ በኋላ፥
17
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦
18
‘አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ አሮኤርን ታልፋለህ፤
19
ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ አትጣላቸው፤ አትውጋቸውም።’
20
ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቈጠረ፤ ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ተቀምጠው ነበረ፤ አሞናውያን ግን “ዘምዞማውያን” ብለው ይጠሩአቸዋል።
21
እነርሱም እንደ ዔናቃውያን ታላቅና ብዙ፥ ጽኑዓንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ከፊታቸው አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ።
22
ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እነርሱ ወረሱአቸው፤ በእነርሱም ፋንታ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።
23
እስከ ጋዛም ድረስ በአሴሮት ተቀምጠው የነበሩትን ኤዋውያንንና ከቀጰዶቅያ የወጡ ቀጰዶቃውያንን አጠፉአቸው፤ በእነርሱም ፋንታ ተቀመጡ።
24
ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፤ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞሬዎናዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን፥ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን ግዛት፤ ውረሳት፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።
25
ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ስምህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፤ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።
26
“ከቄድሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦
27
‘በሀገርህ ላይ ልለፍ፤ በአውራ ጎዳና እሄዳለሁ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አልተላለፍም።
28
የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፤ የምጠጣውንም ውኃ በገንዘብ ስጠኝ፤ በእግሬ ብቻ ልለፍ፤
29
በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች፥ በአሮዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በእግሬ ልለፍ።
30
የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና።
31
እግዚአብሔርም፦ ‘የሐሴቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሴዎንንና ምድሩን በፊትህ በእጅህ አሳልፌ መስጠት እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛ ዘንድ መውረስ ጀምር’ አለኝ።
32
ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊዋጉን ወደ ኢያሳ ወጡ።
33
አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን፤ እርሱንም፥ ልጆቹንም፥ ሕዝቡንም ሁሉ መታን።
34
በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን፤ ከተማውንም ሁሉ፥ ሴቶችንም፥ ሕፃኖችንም አጠፋን፤ አንዳችም የሸሸ በሕይወት አላስቀረንም፥
35
ለእኛ ከማረክናቸው ከብቶቻቸውና ከከተሞቻቸው ከወሰድነው ምርኮ በቀር።
36
በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ተራራ ድረስ ማንኛዪቱም ከተማ አላመለጠችንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን።
37
ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተራራማውም ሀገር ወደ አሉ ከተሞች አልደረስንም።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34