bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Ezekiel 10
Ezekiel 10
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 9
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 11 →
1
እኔም አየሁ፤ እነሆም በኪሩቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር በላያቸው እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ ዙፋን የሚመስል መልክ ተገለጠ።
2
በፍታም የለበሰውን ሰው፥ “በመንኰራኵሮች መካከል በኪሩብ በታች ግባ፤ ከኪሩቤልም መካከል ከአለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ፤ በከተማዪቱም ላይ በትነው” ብሎ ተናገረው። እኔም እያየሁ ገባ።
3
ሰውየውም ሲገባ ኪሩቤል በቤቱ ቀኝ በኩል ቆመው ነበር፤ ደመናውም ውስጠኛውን አደባባይ ሞላ።
4
የእግዚአብሔር ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መድረክ ላይ ቆመ፤ ቤቱም በደመናው ተሞላ፤ አደባባዩም በእግዚአብሔር ክብር ፀዳል ተሞላ።
5
የኪሩቤልም የክንፎቻቸው ድምፅ ሁሉን የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ በሩቅ ይሰማ ነበር።
6
የተቀደሰ በፍታም የለበሰውን ሰው፥ “ከመንኰራኵሮቹ ከኪሩቤል መካከል እሳት ውሰድ” ብሎ በአዘዘው ጊዜ እርሱ ገብቶ በመንኰራኵር አጠገብ ቆመ።
7
ከኪሩቤል መካከልም አንዱ ኪሩብ እጁን በኪሩቤል መካከል ወደ አለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ እሳት ወሰደ፤ የተቀደሰ በፍታም በለበሰው ሰው እጅ አኖረው፤ እርሱም ይዞ ወጣ።
8
ኪሩቤልንም አየሁ፤ ከክንፎቻቸውም በታች የሰው እጅ መሳይ አለ።
9
እኔም አየሁ፤ እነሆም በኪሩቤል አጠገብ አራት መንኰራኵሮች ነበሩ፤ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ፥ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ አጠገብ ነበረ። የመንኰራኵሮቹም መልክ እንደ ቢረሌ ድንጋይ ነበረ።
10
የአራቱም መልክ አንድ ይመስል ነበር፤ መልካቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንደ አለ መንኰራኵር ነበረ።
11
ሲሔዱም በአራቱ ጎድናቸው ይሄዱ ነበር። ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር፤ መጀመሪያው ወደሚያመለክትበት ስፍራ ይሄዱ ነበር፤ ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር።
12
ገላቸውም ሁሉ፥ ጀርባቸውም፥ እጆቻቸውም፤ ክንፎቻቸውም፥ መንኰራኵሮቹም፤ ለአራቱ የነበሩ መንኰራኵሮች በዙሪያቸው ዐይኖች ተሞልተው ነበር።
13
አራቱም መንኰራኵሮች እኔ እየሰማሁ ጌልጌል ተብለው ተጠሩ።
14
ለእያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት፤ አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛውም የሰው ፊት፥ ሦስተኛው የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም የንስር ፊት ነበረ።
15
እነዚህም በኮቦር ወንዝ በእንስሶች አምሳል ያየኋቸው ኪሩቤል በረሩ።
16
ኪሩቤልም ሲሄዱ መንኰራኵሮቹ ከእነርሱ ጋር ተያይዘው ይሄዱ ነበር፤ ኪሩቤልም ይበሩ ዘንድ ክንፋቸውን ከምድር በሚያነሡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር የተያያዘ መንኰራኵራቸው አይመለስም ነበር።
17
የሕይወት መንፈስ በውስጣቸው ነበርና እነዚህ ሲቆሙ እነዚያም ይቆሙ ነበር፤ እነዚህም ሲበርሩ፥ እነዚያ ከእነርሱ ጋር ይበርሩ ነበር።
18
የእግዚአብሔርም ክብር ከቤቱ መድረክ ላይ ወጥቶ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ።
19
ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፤ እኔም እያየሁ ከምድር በረሩ፤ በወጡም ጊዜ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ነበሩ፤ፊት ለፊት በአለው በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በር ዳርቻ ቆሙ፤ የእስራኤልም አምላክ ክብር ከእነርሱ ጋራ በላያቸው ነበረ።
20
ይህ በኮቦር ወንዝ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየሁት እንስሳ ነው፤ ኪሩቤልም እንደ ነበሩ ዐወቅሁ።
21
ለእያንዳንዱ አራት አራት ፊት፥ ለእያንዳንዱም አራት አራት ክንፍ ነበሩት፤ የሰውም እጅ አምሳያ ከክንፎቻቸው በታች ነበረ።
22
ፊቶቻቸውም በኮቦር ወንዝ ከእስራኤል አምላክ ክብር በታች ያየኋቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር፤ እነርሱና መልካቸውም እንዲሁ ነበረ፤ እያንዳንዱም አቅንቶ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።
← Chapter 9
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 11 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48