bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Hosea 5
Hosea 5
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 4
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 6 →
1
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
2
የሚያድኑ አዳኞች ያጠምዱባት ዘንድ ተከሏት፤ እኔ ግን መካሪያችሁ ነኝ።
3
እኔ ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፤ እስራኤልም ከእኔ አልራቀም፤ ኤፍሬም ዛሬ አመንዝሮአልና፤ እስራኤልም ረክሶአልና።
4
ወደ አምላካቸው ይመለሱ ዘንድ ልባቸውን አላቀኑም፤ የዝሙት መንፈስ በውስጣቸው አለና፤ እግዚአብሔርንም አላወቁትምና።
5
የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ ይመሰክራል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በኀጢአታቸው ይደክማሉ፤ ይሁዳም ከእነርሱ ጋር ይደክማል።
6
እግዚአብሔርንም ለመሻት ከበጎቻቸውና ከላሞቻቸው ጋር ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተለይቶአልና አያገኙትም።
7
ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ከድተዋል፤ አሁንም ኵብኵባ እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል።
8
በኮረብታ ላይ መለከትን ንፉ፤ በተራሮችም ላይ ጩኹ፤ ብንያም በተዋረደበት በቤትአዌን ዐዋጅ ንገሩ።
9
ኤፍሬም በዘለፋ ቀን ለጥፋት ይሆናል፤ በእስራኤልም ነገዶች የታመነውን ነገር አሳየሁ።
10
የይሁዳ አለቆች ድምበርን እንደሚያፈርሱ ሆነዋል፤ እኔም መዓቴን እንደ ውኃ አፈስስባቸዋለሁ።
11
ኤፍሬም የተገፋ ሆነ፤ በፍርድም ተረገጠ፤ ከንቱን ይከተል ዘንድ ጀምሮአልና።
12
እኔም ለኤፍሬም እንደ ብል፥ ለይሁዳም ቤት እንደ ነቀዝ እሆንበታለሁ።
13
ኤፍሬምም ደዌውን አያት፤ ይሁዳም ሥቃዩን አያት፤ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈውሳችሁ ዘንድ አልቻለም፤ ከእናንተም ሕማም አልተወገደም።
14
እኔም ለኤፍሬም እንደ ነብር፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ፤ እወስድማለሁ፤ የሚያድናቸውም የለም።
15
እስኪጠፉ ድረስ፥ ፊቴንም እስኪሹ ድረስ እሄዳለሁ፤ ወደ ስፍራዬም እመለሳለሁ።
← Chapter 4
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 6 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14