bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Jeremiah 2
Jeremiah 2
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 51
Chapter 52
Chapter 3 →
1
የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
2
“ሂድ፤ እንዲህ ብለህ በኢየሩሳሌም ጆሮ ተናገር፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት፥ የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ።
3
እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረ፤ የቡቃያው በኵራትም ነበረ፤ የበሉት እንደ በደለኞች ይቈጠራሉ፤ ክፉም ነገር ያገኛቸዋል፤ ይላል እግዚአብሔር።”
4
የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
5
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “አባቶቻችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከንቱነትንም የተከተሉ፥ ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው?
6
እነርሱም፥ “ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳና በባድማ፥ ዕንጨትና ውኃ፥ የእንጨት ፍሬም በሌለበት ምድር፥ ሰው በማያልፍበትና የሰው ልጅም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም።
7
ፍሬዋንና በረከቷንም ትበሉ ዘንድ ወደ ቀርሜሎስ አገባኋችሁ፤ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ።
8
ካህናቱም፦ እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፤ ሕጌን የተማሩትም አላወቁኝም፤ ጠባቂዎችም ዐመፁብኝ፤ ነቢያትም በበዐል ትንቢት ተናገሩ፤ የማይጠቅማቸውንም ነገር ተከተሉ።
9
“ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋር እከራከራለሁ፤ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ።
10
ወደ ኬቲም ደሴቶች እለፉና ተመልከቱ፤ ወደ ቄዳርም ላኩና እጅግ መርምሩ፤ እንደዚህም ያለ ነገር ሆኖ እንደ ሆነ እዩ።
11
አሕዛብ አማልክት ያልሆኑ አማልክቶቻቸውን ይለውጡ አንደ ሆነ እዩ፤ ነገር ግን ሕዝቤ ክብራቸውን ለማይረባ ነገር ለወጡ።
12
ሰማይ በዚህ ደነገጠ፤ እጅግም ተንቀጠቀጠ” ይላል እግዚአብሔር።
13
ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን አድርገዋልና፤ የሕይወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተውኛል፥ የተነደሉትን ውኃውንም ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች ለራሳቸው ቈፍረዋል።
14
“በውኑ እስራኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውላጅ ነውን? ስለ ምን ምርኮ ሆነ?
15
የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፤ በእርሱም ላይ ደነፉ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፤ ከተሞቹንም አፈረሱ፤ የሚቀመጥባቸውም የለም።
16
የሜምፎስና የጣፍናስ ልጆች አስነወሩሽ፤ አላገጡብሽም።
17
ይህን ሁሉ ያመጣብሽ እኔን መርሳትሽ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር አምላክሽ።
18
አሁንስ የግዮንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብፅ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወንዞችንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ?
19
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
20
ከጥንት ጀምሬ ቀንበርሽን ሰብሬአለሁ፤ እስራትሽንም ቈርጫለሁ፤ አንቺም፦ አላገለግልም አልሽ፤ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፤ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
21
እኔ የተመረጠች ወይን፥ ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንዴት መራራ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?
22
በእንዶድ ብትታጠቢም፥ ለራስሽም ሳሙና ብታበዢ፥ በእኔ ፊት በኀጢአትሽ ረክሰሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
23
አንቺስ፦ አልረከስሁም፤ በዓሊምንም አልተከተልሁም፤ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፤ ያደረግሽውንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመንገዶች ትጮኻለች፤
24
በምድረ በዳ ባሉ ውኃዎች ተዘረጋች፤ በሰውነቷም ምኞት ትወሰዳለች፤ ይይዟታል፤ የሚመልሳት ግን የለም፤ የሚሹአትም አይደክሙም፤ በተዋረደችበትም ጊዜ ያገኙአታል።
25
እግርሽን ከሰንከልካላ መንገድ፥ ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ እርስዋ ግን፥ “እጨክናለሁ፤ እንግዶችንም ወድጄአለሁ” ብላ ተከተለቻቸው።
26
ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፤ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች፥ እነርሱና ንጉሦቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ካህናቶቻቸውም፥ ነቢያቶቻቸውም ያፍራሉ።
27
ግንዱን፥ “አንተ አባቴ ነህ፤ ድንጋዩንም፦ አንተ ወለድኸኝ” ይላሉ፤ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፤ በመከራቸው ጊዜ ግን፥ “ተነሥተህ አድነን ይላሉ።
28
ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ፤ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ። በኢየሩሳሌምም በመንገዶችዋ ቍጥር ለጣዖት ሠዉ።
29
“ከእኔ ጋር ለምን ትከራከራላችሁ? ሁላችሁ ክዳችሁኛል፤ ሁላችሁም ዐምፃችሁብኛል” ይላል እግዚአብሔር።
30
ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፤ ተግሣጼን አልተቀበላችሁም፤ ሰይፋችሁ እንደሚሰብር አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል፤ በዚህም አልፈራችሁኝም።
31
የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤስ ስለ ምን፦ እኛ አንገዛልህም፤ ከእንግዲህም ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል?
32
በውኑ ሙሽራ ጌጥዋን ወይስ ድንግል ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ለማይቈጠር ወራት ረስቶኛል።
33
ፍቅርን ለመሻት እንግዲህ በመንገድሽ የምትፈልጊው መልካም ምንድን ነው? እንዲህ አይደለም፤ መንገድሽን ታረክሺ ዘንድ ዳግመኛ በደልሽ።
34
በእጆችሽም የንጹሓን ድሆች ደም ተገኝቶአል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግልጥ አገኘሁት እንጂ በጕድጓድ ፈልጌ አላገኘሁትም።
35
አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፤ በእውነት ቍጣው ከእኔ ይመለስ አልሽ። እነሆ ኀጢአት አልሠራሁም ብለሻልና እፋረድሻለሁ።
36
መንገድሽን እጥፍ ታደርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮጫለሽ? በአሦር እንዳፈርሽ በግብፅም ታፍሪያለሽ።
37
እግዚአብሔርም ተስፋሽን አስቈርጦሻልና፥ በእርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 51
Chapter 52
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52