bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Jonah 3
Jonah 3
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 4 →
1
የእግዚአብሔርም ቃል ሁለተኛ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፦
2
“ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የነገርሁህንም የመጀመሪያውን ስብከት ስበክላት” አለው።
3
ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም ታላቅ ከተማ ነበረች፤ የቅጥርዋም ዙሪያ በእግር የሦስት ቀን መንገድ ያህል ነበረ።
4
ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።”
5
የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።
6
ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ።
7
ዐዋጅም አስነገረ፤ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ፥ “ሰዎችና እንስሶች፥ ላሞችና በጎች አንዳች አይቅመሱ፤ አይሰማሩም፤ ውኃንም አይጠጡ፤
8
ሰዎችና እንስሶችም ማቅ ይልበሱ፤ ወደ እግዚአብሔርም በአንድነት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ከአለው ግፍ ይመለሱ።
9
እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ይምራን፥ ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?”
10
እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4