bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Judges 4
Judges 4
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 5 →
1
የእስራኤል ልጆችም በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ ናዖድ ግን ሞቶ ነበር።
2
እግዚአብሔርም በአሦር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቢን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የሠራዊቱም አለቃ ሲሣራ ነበረ፤ እርሱም በአሕዛብ አሪሶት ይቀመጥ ነበረ።
3
የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና፥ የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት እጅግ ያስጨንቃቸው ነበር።
4
በዚያም ወራት ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ እስራኤልን ትገዛቸው ነበረች።
5
እርስዋም በኤፍሬም ተራራ በቤቴልና በኢያማ መካከል “የዲቦራ ዘንባባ” ተብሎ በሚጠራው ዛፍ ሥር ተቀምጣ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እርስዋ ለፍርድ ይወጡ ነበር።
6
ዲቦራም ልካ ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒሔምን ልጅ ባርቅን ጠርታ እንዲህ አለችው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘህ አይደለምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤
7
እኔም የኢያቢንን ሠራዊት አለቃ ሲሣራን፥ ሰረገሎቹንም፥ ሕዝቡንም ሁሉ ወደ አንተ ወደ ቂሶን ወንዝ እስባለሁ፤ በእጅህም አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”
8
ባርቅም፥ “አንቺ ከእኔ ጋር ብትሄጂ እኔ እሄዳለሁ፤ አንቺ ግን ከእኔ ጋር ባትሄጂ እኔ አልሄድም፤ እግዚአብሔር መልአኩን ከእኔ ጋር የሚልክበትን ዕለት አላውቃትምና” አላት።
9
ዲቦራም፥ “በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን በሴት እጅ አሳልፎ ይሰጣልና በዚህ በምትሄድበት መንገድ ለአንተ ክብር አይሆንም” አለችው። ዲቦራም ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች።
10
ባርቅም ዛብሎንንና ንፍታሌምን ወደ ቃዴስ ጠራቸው፤ ዐሥር ሺህም ሰዎች ተከትለውት ወጡ፤ ዲቦራም ከእርሱ ጋር ወጣች።
11
ቄናዊውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኢዮባብ ልጆች ከቄናውያን ተለይቶ ድንኳኑን በቃዴስ አጠገብ እስከ ነበረው ታላቅ ዛፍ ድረስ ተከለ።
12
የአቢኒሔምም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደ ወጣ ለሲሣራ ነገሩት።
13
ሲሣራም ሰረገሎቹን ሁሉ፥ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች፥ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ሕዝቡን ሁሉ ከአሕዛብ አሪሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰባቸው።
14
ዲቦራም ባርቅን፥ “እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር በፊትህ ይሄዳል” አለችው። ባርቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ።
15
እግዚአብሔርም ሲሣራን፥ ሰረገሎቹንም ሁሉ፥ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፤ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ።
16
ባርቅም ሰረገሎችንና ሠራዊቱን እስከ አሕዛብ አሪሶት ድረስ አባረረ፤ የሲሣራም ሠራዊት ሁሉ በሰይፍ ስለት ወደቀ፤ አንድ እንኳ አልቀረም።
17
ሲሣራም ወደ ጓደኛው ወደ ቄናዊው ወደ ሔቤር ሚስት ወደ ኢያዔል ድንኳን በእግሩ ሸሸ፤ በአሶር ንጉሥ በኢያቢንና በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ነበርና።
18
ኢያዔልም ሲሣራን ለመቀበል ወጥታ፥ “ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፤ አትፍራም” አለችው። ወደ እርስዋም ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ በምንጣፍም ሸፈነችው።
19
ሲሣራም፥ “ጠምቶኛልና እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጪኝ” አላት፤ እርስዋም የወተቱን ዕቃ ፈትታ አጠጣችው፤ ፊቱንም ሸፈነችው።
20
እርሱም፥ “ከድንኳኑ ደጃፍ ቁሚ፤ ሰውም መጥቶ፦ ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠይቅሽ አንቺ፦ ‘የለም’ ትዪዋለሽ” አላት።
21
የሔቤርም ሚስት ኢያዔል የድንኳኑን ካስማ ወሰደች፤ በሁለተኛ እጅዋም መዶሻ ያዘች፤ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረበች፤ በጆሮ ግንዱም ካስማውን ቸነከረችበት፤ እርሱም ደክሞ አንቀላፍቶ ነበርና ካስማው ወደ መሬት ጠለቀ፤ እርሱም ከእግርዋ በታች ተንፈራፈረ፤ ተዘርሮም ሞተ።
22
እነሆም፥ ባርቅ ሲሣራን ሲያባርር ኢያዔል ልትገናኘው ወጥታ፥ “ና፤ የምትሻውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው። ወደ እርስዋም ገባ፤ እነሆም፥ ሲሣራን ወድቆ፥ ሞቶም አገኘው፤ ካስማውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ነበረ።
23
በዚያም ቀን እግዚአብሔር የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢንን በእስራኤል ልጆች ፊት አዋረደው።
24
የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢንንም እስኪያጠፉ ድረስ በከነዓን ንጉሥ በኢያቢን ላይ የእስራኤል ልጆች እጅ እየበረታች ሄደች።
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 5 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21