bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
/
1 John 1
1 John 1
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 2 →
1
ከመጀመሪያው የነበረውን፥ የሰማነውን፥ በዐይኖቻችንም ያየነውን፥ የተመለከትነውንና እጆቻችንም የዳሰሱትን፥ ስለ ሕይወት ቃል እንናገራለን፤
2
ሕይወትም ተገለጠ፥ አይተነዋል እንመሰክራለንም፥ በአብ ዘንድ የነበረውን ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤
3
እናንተም ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን። ኅብረታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
4
ደስታችን ሙሉ እንዲሆን ይህን እንጽፍላችኋለን።
5
ከእርሱ የሰማነውና ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት ይህ ነው፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም።
6
ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን እያልን በጨለማ ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤
7
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
8
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ዘንድ የለም።
9
ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን የታመነና ጻድቅ ነው፥ ከዓመፃም ሁሉ ያነጻናል።
10
ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 2 →
All chapters:
1
2
3
4
5