bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
/
2 John 1
2 John 1
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
Jump to:
Chapter 1
1
ሽማግሌው፥ ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆችዋ፥ በእውነት ለምወዳቸው፥ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወዱአቸው፥
2
በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘለዓለም ስለሚሆን እውነት፥
3
ከእግዚአብሔር አብና በእውነትና በፍቅር የአብ ልጅ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ ምሕረትና ሰላም ከእኛ ጋር ይሁን።
4
ከልጆችሽ አንዳንዶቹ ከአባት እንደተቀበልነው ትእዛዝ መሠረት በእውነት የሚመላለሱ ሆነው በማግኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል።
5
አሁንም እመቤት ሆይ! አዲስን ትእዛዝ አልጽፍልሽም ነገር ግን ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረውን ነው፥ ይህም እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ።
6
ፍቅር ይህ ነው፥ እርሱም በትእዛዛቱ መመላለስ ነው፤ ትእዛዙ ይህ ነው፥ ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደ ሰማችሁት፥ በእርሱ ተመላለሱ።
7
ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና፤ እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህም አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።
8
የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ነገር ግን ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
9
በክርስቶስ ትምህርት የማይኖርና የሚወጣ ሰው ሁሉ አምላክ የለውም፤ በዚህ ትምህርት የሚኖር ግን አብና ወልድ አሉት።
10
ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤
11
ሰላም የሚለው የክፉ ሥራው ተካፋይ ይሆናል።
12
ብዙ የምጽፍላችሁ ነገር ነበረኝ፤ ነገር ግን በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልፈለግሁም፤ ዳሩ ግን ደስታችን ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ መጥቼ ፊት ለፊት ላናግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
13
የተመረጠችው የእኅትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል።
Jump to:
Chapter 1
All chapters:
1