bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
/
Exodus 27
Exodus 27
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
← Chapter 26
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 28 →
1
“ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ሥራ፤ መሠዊያው አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ይሁን።
2
በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አድርግለት፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ፤ በነሐስም ለብጠው።
3
አመድ የሚጠራቀምባቸውን ምንቸቶች፥ መጫሪያዎቹን፥ ድስቶቹን፥ ሜንጦቹንና ማንደጃዎቹን ታደርጋለህ፤ ዕቃዎቹ ሁሉ ከነሐስ ሥራ።
4
እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የነሐስ መከታ አድርግለት፤ ለመከታውም አራት የነሐስ ቀለበት በአራቱም ማዕዘን አድርግለት።
5
መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ እንዲደርስ ከመሠዊያው እርከን በታች አድርገው።
6
ለመሠዊያው ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሥራ፥ በነሐስም ለብጣቸው።
7
መሎጊያዎቹ በቀለበቶቹ ውስጥ ይግቡ፥ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎቹ በሁለቱ ጎኖች ይሁኑ።
8
ከሳንቃዎች ሠርተህ ባዶ አድርገው፤ በተራራው እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንዲሁ ይሥሩት።
9
“የማደሪያውን አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ በኩል ከጥሩ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ይሁኑ፥ የአንዱ ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤
10
ሀያ ምሰሶዎቹና ሀያ እግሮቹ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ፤ የምሶሶቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ይሁኑ።
11
እንዲሁም በሰሜን በኩል መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ከነሐስ የተሠሩ ሀያ ምሰሶዎች እና ሀያ እግሮች ይሁኑ፥ ለምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ።
12
በምዕራብ በኩል ላለው ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር እግሮች ይሁኑ።
13
በምሥራቅ በኩል ያለው የአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ይሁን።
14
በአንድ በኩል ያለው የመጋረጃዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ፥ ምሰሶዎቹ ሦስት፥ እግሮቹ ሦስት ይሁን።
15
በሌላውም በኩል የመጋረዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ፥ ምሰሶዎቹ ሦስት፥ እግሮቹም ሦስት ይሁን።
16
ለአደባባዩም መግቢያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ የተጠለፈ ሀያ ክንድ መጋረጃ ይሁን፤ ምሰሶዎቹ አራት፥ እግሮቹም አራት ይሁኑ።
17
በአደባባዩም ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ በብር ይያያዙ፥ ኩላቦቻቸው ከብር እግሮቻቸው ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።
18
የአደባባዩ ርዝመት መቶ ክንድ፥ ስፋቱ አምሳ ክንድ ይሁን፥ ከፍታው አምስት ክንድ ይሁን፥ መጋረጃውም ከጥሩ በፍታ፥ እግሮቹም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።
19
ለአገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፥ ካስማዎቹ ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ፥ የነሐስ ይሁኑ።
20
“መብራቱ ሁልጊዜ እንዲበራ ለመብራት የሚሆን ተጨምቆ የተጠለለ ንጹሕ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው።
21
ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”
← Chapter 26
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 28 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40