bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
/
Mark 3
Mark 3
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 4 →
1
ኢየሱስ እንደገና ወደ ምኵራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር፤
2
እነርሱም በሰንበት ይፈውሰው እንደሆነ አይተው ሊከስሱት ፈልገው ይጠባበቁት ነበር።
3
እርሱም እጁ የሰለለችውን ሰው “ተነሥ! በመካከል ቁም” አለው።
4
ከዚያም “በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዷልን? ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል?” ሲል ጠየቃቸው፤ እነርሱ ግን ዝም አሉ።
5
ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ፥ ዙሪያውን በቁጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። እርሱም ዘረጋ፤ እጁም ዳነች።
6
ፈሪሳውያንም ወጥተው ወዲያው እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ተማከሩበት።
7
ኢየሱስም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ባሕር ፈቀቅ አለ፤ ከገሊላና ከይሁዳ የመጡም ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤
8
ያደረገውን ነገር ሁሉ ሰምተው፥ ከኢየሩሳሌም፥ ከኤዶምያስ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ፥ ከጢሮስና ከሲዶና አካባቢ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ።
9
ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ እንዳያስጨንቁት ጀልባ እንዲያዘጋጁለት ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፤
10
ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ በሕመም የሚሠቃዩ ሁሉ በእጃቸው ሊነኩት ፈልገው ያጨናንቁት ነበር።
11
ርኩሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” እያሉ ጮኹ።
12
እርሱም ማንነቱን እንዳይገልጡ በጥብቅ ገሠጻቸው።
13
ወደ ተራራም ወጣ፤ ራሱም የፈለጋቸውን ወደ እርሱ ጠራ፤ ወደ እርሱም ሄዱ።
14
ከእርሱም ጋር እንዲሆኑና ለመስበክም እንዲልካቸው ዐሥራ ሁለቱን መርጦ “ሐዋርያት” አላቸው።
15
አጋንንትን እንዲያስወጡም ሥልጣን ሰጣቸው።
16
የተመረጡት ዐሥራ ሁለቱም፦ ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው ስምዖን፤
17
ቦአኔርጌስ፥ ማለትም የነጐድጓድ ልጆች ብሎ የሰየማቸው የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና የያዕቆብ ወንድም ዮሐንስን፤
18
እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ በርተሎሜውስ፥ ማቴዎስ፥ ቶማስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ታዴዎስ፥ ቀነናዊው ስምዖን፥
19
እና አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ናቸው።
20
ከዚያም ወደ ቤት ገቡ፤ ምግብ መመገብ እንኳ እስኪያቅታቸው ድረስ እንደገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ።
21
ዘመዶቹም “አእምሮውን ስቷል” ሲባል ሰምተው ሊይዙት መጡ።
22
ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጸሐፍትም “በብዔልዜቡል ተይዟል! ደግሞም በዚህ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል!” ብለው ተናገሩ።
23
እነርሱንም ወደ እርሱ ጠርቶ በምሳሌ እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣን ሰይጣንን ሊያስወጣ እንዴት ይችላል?
24
መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤
25
እንዲሁም አንድ ቤተሰብ እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤተሰብ ሊቆም አይችልም።
26
ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ቢነሣና ቢለያይ መጨረሻው ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም።
27
ነገር ግን ወደ ኀይለኛው ቤት ገብቶ አስቀድሞ ኀይለኛውን ሳያስር ንብረቱን መዝረፍ የሚችል የለም፤ ያንጊዜ ግን ቤቱን ይዘርፋል።
28
“በእውነት እላችኋለሁ፤ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ፥ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤
29
በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘለዓለም ጥፋት ይሆንበታል እንጂ ለዘለዓለም አይሰረይለትም።”
30
ምክንያቱም “ርኩስ መንፈስ አለበት፤” ብለዋል።
31
የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ ወደ እርሱ መጡ፤ በውጪም ቆመው ወደ እርሱ ሰው ላኩና አስጠሩት።
32
ብዙ ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠው ነበሩና “እነሆ፥ እናትህ፥ ወንድሞችህና እኅቶችህ በውጭ ቆመው ይፈልጉሃል፤” አሉት።
33
እርሱም “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቃቸው።
34
በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም እየተመለከተ፥ “እነሆ! እናቴና ወንድሞቼ!
35
የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ፥ እኅቴም፥ እናቴም ነው” አለ።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16