bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
/
Song of Solomon 3
Song of Solomon 3
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 4 →
1
ሌሊት በመኝታዬ ላይ ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፥ ፈለግሁት አላገኘሁትም።
2
እነሣለሁ በከተማይቱም እዞራለሁ፥ ነፍሴ የወደደችውን በጎዳናና በአደባባይ እፈልጋለሁ፥ ፈለግሁት አላገኘሁትም።
3
ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸውም።
4
ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም ወደ እናቴም ቤት ወደ ወለደችኝም እልፍኝ እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።
5
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈንጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥ ፍቅርን እንዳታስነሡትና እንዳታነሣሡት በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አስምላችኋለሁ።
6
መዓዛም እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነችው፥ ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ሁሉ የሆነችው፥ ይህች ከምድረበዳ እንደ ጢስ ምስሶ የወጣችው ማን ናት?
7
እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፥ ከእስራኤል ኃያላን መካከል ስድሳ ኃያላን በዙሪያው ናቸው።
8
ሁሉም ሰይፍ የያዙና ጦርነት የለመዱ ናቸው፥ በሌሊት ከሚከሰት አደጋ የተነሣ ሰው ሁሉ ሰይፉ በወገቡ አለ።
9
ንጉሡ ሰሎሞን መቀመጫ ከሊባኖስ እንጨት ለራሱ አሠራ።
10
ምሰሶቹን የብር፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥ መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፥ ውስጡ በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ፍቅር የተለበጠ ነው።
11
እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት፥ ውጡ፥ እናቱ በሰርጉ ቀንና በልቡ ደስታ ቀን ያደረገችለትን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን እዩ።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8