bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
1 Kings 4
1 Kings 4
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 5 →
1
ንጉሥ ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤
2
ዋና ዋናዎቹ ሹማምቱም እነዚህ ነበሩ፤ የሳዶቅ ልጅ ዓዛርያስ፣ ካህን፤
3
የሺሻ ልጆች ኤሊሖሬፍና አኪያ፣ ጸሓፊዎች፤ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣ ታሪክ ጸሓፊ፤
4
የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ የሰራዊቱ ዋና አዛዥ፤ ሳዶቅና አብያታር፣ ካህናት፤
5
የናታን ልጅ ዓዛርያስ፣ የአውራጃ ገዦች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ዛቡድ፣ ካህንና የንጉሡ የቅርብ አማካሪ፤
6
አሒሳር፣ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፤ የዓብዳ ልጅ አዶኒራም የግዳጅ ሥራ ተቈጣጣሪ።
7
እንዲሁም ሰሎሞን ለንጉሡና ለንጉሡ ቤት የሚሆነውን ቀለብ ከመላው እስራኤል የሚሰበስቡ ዐሥራ ሁለት የአውራጃ ገዦች ነበሩት፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ የወር ቀለብ የሚያቀርቡ ነበሩ።
8
ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ ቤንሑር፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር፤
9
ቤንጼቄር፣ በማቃጽ፣ በሻዓልቢም፣ በቤትሳሜስ፣ በኤሎንቤትሐናን፤
10
ቤንሔሴድ፣ በአሩቦት ውስጥ የሚገኙት ሰኰትና የኦፌር አገር በሙሉ የእርሱ ነበር፤
11
ቤን አሚናዳብ፤ በናፎት ዶር፣ እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ጣፈትን አግብቶ የነበረ ነው፤
12
የአሒሉድ ልጅ በዓና፣ በታዕናክና በመጊዶ እንዲሁም ከጻርታን ቀጥሎ ቍልቍል እስከ ኢይዝራኤል ባለው በቤትሳን ሁሉ፣ ከዚያም ዮቅምዓምን ተሻግሮ እስከ አቤልምሖላና ድረስ፣
13
ቤንጌበር፣ በገለዓድ ራሞት ከተማ እዚያው ገለዓድ ውስጥ የምናሴ ልጅ የኢያዕር መንደሮች፣ በባሳንም የአርጎብ አውራጃ እንዲሁም በሮቻቸው የናስ መወርወሪያ በሆኑ ስድሳ ባለ ቅጥር ታላላቅ ከተሞች፤
14
የዒዶ ልጅ አሒናዳብ፤ በማሃናይም፣
15
አኪማአስ በንፍታሌም፣ እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ባስማትን አግብቶ የነበረ ነው፤
16
የኩሲ ልጅ በዓና፤ በአሴርና በበዓሎት፣
17
የፋሩዋ ልጅ ኢዮሣፍጥ በይሳኮር፣
18
የኤላ ልጅ ሳሚ በብንያም፣
19
የኡሪ ልጅ ጌበር፤ በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣ በባሳን ንጉሥ በዐግ አገር፣ እርሱም የአውራጃው ብቸኛ ገዥ ነበር።
20
የይሁዳና የእስራኤል ሕዝቦች ብዛታቸው እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ሆነ፤ ይበሉ፣ ይጠጡና ይደሰቱም ነበር።
21
ሰሎሞንም ከወንዙ አንሥቶ እስከ ፍልስጥኤማውያን ምድር፣ ከዚያም እስከ ግብፅ ዳርቻ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ ገዛ፤ እነዚህም አገሮች ግብር አመጡለት፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ተገዙለት።
22
ለሰሎሞን በየቀኑ የሚገባለትም ቀለብ ይህ ነበር፤ ሠላሳ ኮር ማለፊያ ዱቄት፣ ስድሳ ኮር መናኛ ዱቄት፣
23
ዐሥር ቅልብ ሰንጋዎች፣ ሃያ ግጦሽ መሬት ላይ የሚውሉ በሬዎች፣ መቶ በግና ፍየል እንዲሁም ዋሊያ፣ ሚዳቋ፣ የበረሓ ፍየልና ምርጥ አዕዋፍ።
24
ከወንዙ በስተ ምዕራብ፣ ከቲፍሳ እስከ ጋዛ ያሉትን መንግሥታት ስለ ገዛ፣ በሁሉም አቅጣጫ ሰላም ሆኖለት ነበር።
25
በሰሎሞን ዘመን ሁሉ ከዳን አንሥቶ እስከ ቤርሳቤህ ያለው ይሁዳና እስራኤል፣ እያንዳንዱ ሰው ከወይኑና ከበለሱ ጥላ ሥር በሰላም ለመኖር በቃ።
26
ሰሎሞን ሠረገላ የሚጐትቱ ፈረሶች የሚያድሩበት አራት ሺሕ ጋጣና ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት ።
27
የየአውራጃው ሹማምትም በየወር ተራቸው ንጉሡን ሰሎሞንንና ወደ ንጉሡ ማእድ የሚቀርቡትን ሁሉ ምንም ሳያጓድሉ ይቀልቡ ነበር፤
28
እንዲሁም ለሠረገላ ፈረሶችና ለፈጣን ፈረሶች የተመደበውን ገብስና ጭድ ከተፈለገው ቦታ ድረስ ያመጡ ነበር።
29
አምላክ ለሰሎሞን ጥበብንና እጅግ ታላቅ ማስተዋልን እንዲሁም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋትን ሰጠው።
30
የሰሎሞን ጥበብ ከምሥራቅ ሰዎች ሁሉ ጥበብ በጣም የላቀ ከግብፅም ጥበብ ሁሉ የበለጠ ነበር፤
31
እርሱም ከማንም ሰው ይልቅ ጥበበኛ ነበር፣ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታን፣ ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ደግሞም ከደራል ይልቅ ጥበበኛ ነበር፤ ዝናውም በዙሪያው ባሉት አሕዛብ ሁሉ ተሰማ።
32
እርሱም ሦስት ሺሕ ምሳሌዎችን ተናገረ፤ የመሓልዩም ቍጥር ሺሕ አምስት ነበር።
33
ከሊባኖስ ዝግባ አንሥቶ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ስለ ዕፀዋት ተናግሯል፤ እንዲሁም ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በሆዳቸው ስለሚሳቡ እንስሳትና ስለ ዓሦችም ተናግሯል፤
34
ጥበቡን ከሰሙት ከዓለም ነገሥታት ሁሉ የተላኩ፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ የሰሎሞንን ጥበብ ለማድመጥ መጡ።
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 5 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22