bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
1 Samuel 3
1 Samuel 3
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 4 →
1
ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይታይም ነበር።
2
ዐይኖቹ ከመድከማቸው የተነሣ ማየት የተሳነው ዔሊ አንድ ሌሊት በስፍራው ተኝቶ ነበር።
3
ሳሙኤልም ደግሞ የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ የእግዚአብሔር መብራትም ገና አልጠፋም ነበር።
4
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ጠራው። ሳሙኤልም፣ “እነሆኝ” አለ፤
5
ወደ ዔሊም ሮጦ በመሄድ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው። ዔሊ ግን፣ “እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው፤ እርሱም ሄዶ ተኛ።
6
ደግሞም እግዚአብሔር ፣ “ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሣና ወደ ዔሊ ሄዶ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው። ዔሊም መልሶ፣ “ልጄ ሆይ፤ እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው።
7
በዚያም ጊዜ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ገና አላወቀም ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር።
8
እግዚአብሔር ሳሙኤልን ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው፤ አሁንም ሳሙኤል ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው። ዔሊ በዚህ ጊዜ ብላቴናውን ይጠራ የነበረው እግዚአብሔር መሆኑን ተረዳ።
9
በዚያ ጊዜ ዔሊ ሳሙኤልን፣ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፣ ‘ እግዚአብሔር ሆይ፤ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ስለዚህም ሳሙኤል ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ።
10
እግዚአብሔርም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ ቀደም ሲል እንዳደረገው ሁሉ “ሳሙኤል! ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፣ “ባሪያህ ይሰማልና ተናገር” አለ።
11
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፤ የሰሚውን ሁሉ ጆሮ ጭው የሚያደርግ አንድ ነገር በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ።
12
በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተ ሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ።
13
ዔሊ በሚያውቀው ኀጢአት ምክንያት በቤተ ሰቡ ላይ ለዘላለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር፤ ልጆቹ አስጸያፊ ነገር አድርገዋል ፤ እርሱ ግን አልከለከላቸውም።
14
ስለዚህ ‘የዔሊ ቤት በደል በመሥዋዕትም ሆነ በቍርባን ፈጽሞ አይሰረይም’ ብዬ በዔሊ ቤት ላይ ምያለሁ።”
15
ሳሙኤል እስኪነጋ ድረስ ተኛ፤ ከዚያም ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ ራእዩንም ለዔሊ መንገር ፈራ፤
16
ዔሊ ግን ሳሙኤልን፣ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም፣ “እነሆኝ” ሲል መለሰ።
17
ዔሊም፣ “ እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? አትደብቀኝ፤ ከነገረህ ውስጥ አንዲቱን እንኳ ብትደብቀኝ እግዚአብሔር እንደዚያው ያድርግብህ፤ ከዚያ ለከፋም ይዳርግህ” አለው።
18
ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፣ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ” አለ።
19
ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ፣ ከሚናገረው ቃል አንዳች በምድር አይወድቅም ነበር።
20
ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል በርግጥ የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን ዐወቁ።
21
እግዚአብሔር በሴሎ ይገለጥ ነበር፤ በዚያም በቃሉ አማካይነት ራሱን ለሳሙኤል ገለጠ።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31