bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Thessalonians 3
2 Thessalonians 3
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
1
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ፤ በእናንተ ዘንድ እንደ ሆነው የጌታ ቃል በፍጥነት እንዲሠራጭና እንዲከበር ለእኛ ጸልዩልን፤
2
ደግሞም ሰው ሁሉ እምነት ያለው ስለማይሆን ከዐመፀኞችና ከክፉ ሰዎች እንድንድን ጸልዩልን።
3
ጌታ ግን ታማኝ ነው፤ እርሱም ያበረታችኋል፤ ከክፉውም ይጠብቃችኋል።
4
እኛ ያዘዝናችሁን አሁን አደረጋችሁ፤ ወደ ፊትም እንደምታደርጉ በጌታ እንታመናለን።
5
ጌታ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ወደ ክርስቶስ ጽናት ይምራው።
6
ወንድሞች ሆይ፤ ሥራ ፈት ከሆነና ከእኛ በተቀበላችሁት ትምህርት መሠረት ከማይኖር ወንድም እንድትርቁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን፤
7
የእኛን ምሳሌ እንዴት መከተል እንደሚገባችሁ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና። ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ ሥራ ፈቶች አልነበርንም፤
8
ደግሞም የማንንም እንጀራ በነጻ አልበላንም፤ ነገር ግን ከእናንተ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን እንደክምና እንሠራ ነበር፤
9
ይህን ያደረግነው ምሳሌነታችንን እንድትከተሉ ብለን እንጂ የሚያስፈልገንን ነገር ከእናንተ ለማግኘት ሥልጣን ሳይኖረን ቀርቶ አይደለም።
10
ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ፣ “ሊሠራ የማይወድድ አይብላ” ብለን ይህን ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበርና።
11
ከእናንተ አንዳንዶች ሥራ ፈቶች እንደ ሆኑ ሰምተናል፤ እነርሱም ያለ ሥራ እየዞሩ በሰው ጕዳይ ጣልቃ የሚገቡ ናቸው።
12
እንደዚህ ያሉ ሰዎች ተግተው ሥራቸውን እንዲሠሩና እንጀራቸውን እንዲበሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም።
13
እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፤ መልካም ሥራን ከመሥራት ከቶ አትታክቱ።
14
በዚህ መልእክት ላይ ላለው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፣ እንደዚህ ያለውን ሰው በጥንቃቄ ተከታተሉት፤ በሥራውም እንዲያፍር ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።
15
ሆኖም እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።
16
የሰላም ጌታ ራሱ በሁሉም ነገር ዘወትር ሰላም ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
17
ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ የመልእክቶቼም ሁሉ መለያ ይህ ነው፤ አጻጻፌም እንደዚህ ነው።
18
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
All chapters:
1
2
3