bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Amos 3
Amos 3
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 4 →
1
የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ እግዚአብሔር በእናንተ ከግብፅ ባወጣሁት ሕዝብ ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤
2
“ከምድር ወገን ሁሉ፣ እናንተን ብቻ መረጥሁ፤ ስለዚህ ስለ ሠራችሁት ኀጢአት ሁሉ፣ እኔ እቀጣችኋለሁ።”
3
በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ፣ አብረው መጓዝ ይችላሉን?
4
አንበሳ የሚበላውን ሳያገኝ፣ በጫካ ውስጥ ይጮኻልን? ምንም ነገርስ ሳይዝ፣ በዋሻው ውስጥ ያገሣልን?
5
ወጥመድ ሳይዘረጋ፣ ወፍ በምድር ላይ ይጠመዳልን? የሚይዘው ነገር ሳይኖርስ፣ ወጥመዱ ከምድር ይፈነጠራልን?
6
የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?
7
በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምስጢሩን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሳይገልጥ፣ ምንም ነገር አያደርግም።
8
አንበሳ አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?
9
ለአዛጦን ምሽግ፣ ለግብፅም ምሽግ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጧ ያለውን ታላቅ ሁከት፣ በሕዝቧም መካከል ያለውን ግፍ እዩ።”
10
“ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣ በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤” ይላል እግዚአብሔር ።
11
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጠላት ምድሪቱን ይወርራል፤ ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል፤ ድንኳኖቻችሁን ይዘርፋል።”
12
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ፣ ሁለት የእግር ዐጥንት ወይም የጆሮ ቍራጭ እንደሚያድን፣ እንዲሁም በሰማርያ በዐልጋቸው ጫፍ ላይ፣ በደማስቆም በምንጣፋቸው ላይ የተቀመጡ፣ እስራኤላውያን ይድናሉ።”
13
“ይህን ስሙ፤ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ” ይላል ጌታ፣ ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር ።
14
“እስራኤልን ስለ ኀጢአቷ በምቀጣበት ቀን፣ የቤቴልን መሠዊያዎች አፈርሳለሁ፤ የመሠዊያው ቀንዶች ይቈረጣሉ፤ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።
15
የክረምቱን ቤት፣ ከበጋው ቤት ጋር እመታለሁ፤ በዝኆን ጥርስ ያጌጡ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፤ ታላላቅ አዳራሾችም ይፈርሳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር ።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9