bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Ezra 2
Ezra 2
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 3 →
1
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው መካከል ከምርኮ ተመልሰው ወደ የራሳቸው ከተሞች፣ ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የአገሩ ልጆች እነዚህ ናቸው፤
2
የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከሠራያ፣ ከረዕላያ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከመሴፋር፣ ከበጉዋይ፣ ከሬሁም፣ ከበዓና ጋር ነበር። የተመለሱት የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦
3
የፋሮስ ዘሮች 2,172
4
የሰፋጥያስ ዘሮች 372
5
የኤራ ዘሮች 775
6
ከኢያሱና ከኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,812
7
የኤላም ዘሮች 1,254
8
የዛቱዕ ዘሮች 945
9
የዘካይ ዘሮች 760
10
የባኒ ዘሮች 642
11
የቤባይ ዘሮች 623
12
የዓዝጋድ ዘሮች 1,222
13
የአዶኒቃም ዘሮች 666
14
የበጉዋይ ዘሮች 2,056
15
የዓዲን ዘሮች 454
16
የሕዝቅያስ ልጅ የአጤር ዘሮች 98
17
የቤሳይ ዘሮች 323
18
የዮራ ዘሮች 112
19
የሐሱም ዘሮች 223
20
የጋቤር ዘሮች 95
21
የቤተ ልሔም ሰዎች 123
22
የነጦፋ ሰዎች 56
23
የዓናቶት ሰዎች 128
24
የዓዝሞት ዘሮች 42
25
የቂርያትይዓሪም ፣ የከፊራና የብኤሮት ዘሮች 743
26
የራማና የጌባ ዘሮች 621
27
የማክማስ ሰዎች 122
28
የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223
29
የናባው ዘሮች 52
30
የመጌብስ ዘሮች 156
31
የሌላው ኤላም ዘሮች 1,254
32
የካሪም ዘሮች 320
33
የሎድ፣ የሐዲድና 725
34
የኢያሪኮ ሰዎች 345
35
የሴናዓ ዘሮች 3,630
36
ካህናቱ፦ ከኢያሱ ቤተ ሰብ የዮዳኤ ዘሮች 973
37
የኢሜር ዘሮች 1,052
38
የፋስኮር ዘሮች 1,247
39
የካሪም ዘሮች 1,017
40
ሌዋውያኑ፦ በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ዘሮች 74
41
መዘምራኑ፦ የአሳፍ ዘሮች 128
42
የቤተ መቅደሱ በረኞች፦ የሰሎም፣ የአጤር፣ የጤልሞን፣ የዓቁብ፣ የሐጢጣና የሶባይ ዘሮች 139
43
የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦ የሲሐ፣ የሐሡፋና የጠብዖት ዘሮች፤
44
የኬራስ፣ የሲዓ፣ የፋዶን ዘሮች፤
45
የልባና፣ የአጋባ፣ የዓቁብ ዘሮች፤
46
የአጋብ፣ የሰምላይ፣ የሐናን ዘሮች፤
47
የጌዴል፣ የጋሐር፣ የራያ ዘሮች፤
48
የረአሶን፣ የኔቆዳ፣ የጋሴም ዘሮች፤
49
የዖዛ፣ የፋሴሐ፣ የቤሳይ ዘሮች፤
50
የአስና፣ የምዑናውያን፣ የንፉሰሲም ዘሮች፤
51
የበቅቡቅ፣ የሐቁፋ፣ የሐርሑር ዘሮች፤
52
የበስሎት፣ የምሒዳ፣ የሐርሳ ዘሮች፤
53
የበርቆስ፣ የሲሣራ፣ የቴማ ዘሮች፤
54
የንስያና የሐጢፋ ዘሮች።
55
የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦ የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፤
56
የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጌዴል ዘሮች፤
57
የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣ የፈክራት ሐፂቦይም፣ የአሚ ዘሮች፤
58
392
59
ከዚህ የሚከተሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር ከተሞች የመጡ ናቸው፤ ነገር ግን ቤተ ሰቦቻቸው የእስራኤል ዘር መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦
60
የዳላያ፣ የጦብያና የኔቆዳ ዘሮች 652
61
ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስና የቤርዜሊ ዘሮች፤ ቤርዜሊ በዚህ ስም ሊጠራ የቻለው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ልጅ አግብቶ ስለ ነበር ነው።
62
እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ማግኘት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው፣ ከክህነት አገልግሎት ተገለሉ።
63
አገረ ገዥውም በኡሪምና በቱሚም እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ካህን እስኪነሣ ድረስ፣ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።
64
ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ብዛት 42,360 ነበረ፤
65
ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 200 ወንድና ሴት ዘማሪዎችም ነበሯቸው።
66
736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣
67
435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው።
68
በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተ ሰብ መሪዎች በቀድሞው ቦታ እንደ ገና ለሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት በበጎ ፈቃድ ስጦታ አደረጉ።
69
እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ ፣ 5,000 ምናን ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
70
ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየከተሞቻቸው ተቀመጡ።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10