bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Hosea 6
Hosea 6
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 5
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 7 →
1
“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰባብሮናል፤ እርሱም ይጠግነናል፤ እርሱ አቍስሎናል፤ እርሱም ይፈውሰናል።
2
ከሁለት ቀን በኋላ ያነቃናል፤ በእርሱም ፊት እንድንኖር፣ በሦስተኛው ቀን ያስነሣናል።
3
እግዚአብሔርን እንወቀው፤ የበለጠ እናውቀውም ዘንድ እንትጋ፤ እንደ ንጋት ብርሃን፣ በርግጥ ይገለጣል፤ ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣ እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
4
“ኤፍሬም ሆይ፤ ምን ላድርግህ? ይሁዳ ሆይ፤ ምን ላድርግህ? ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ጉም፣ እንደሚጠፋም የጧት ጤዛ ነው።
5
ስለዚህ በነቢያቴ ቈራረጥኋችሁ፤ በአፌም ቃል ገደልኋችሁ፣ ፍርዴም እንደ መብረቅ በላያችሁ አበራ።
6
ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፣ ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እሻለሁና።
7
እንደ አዳም ቃል ኪዳንን ተላለፉ፤ በዚያም ለእኔ ታማኝ አልነበሩም።
8
ገለዓድ በደም የተበከለች፣ የክፉዎች ሰዎች ከተማ ናት።
9
ወንበዴዎች ሰውን ለማጥቃት እንደሚያደቡ፣ ካህናትም በቡድን እንዲሁ ያደርጋሉ፤ በሴኬም መንገድ ላይ ሰዎችን ይገድላሉ፤ አሳፋሪም ወንጀል ይፈጽማሉ።
10
በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ ኤፍሬም ዘማዊ ሆነ፤ እስራኤልም ረከሰ።
11
“ይሁዳ ሆይ፤ ለአንተም፣ መከር ተመድቦብሃል። “ሕዝቤን ከምርኮ አገር በመለስሁ ጊዜ፣
← Chapter 5
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 7 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14