bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Jeremiah 4
Jeremiah 4
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 51
Chapter 52
Chapter 5 →
1
“እስራኤል ሆይ፤ ብትመለስ፣ ወደ እኔ ብትመለስ” ይላል እግዚአብሔር ፤ “አስጸያፊ ነገሮችህን ከፊቴ ብታስወግድ፣ ባትናወጥ ብትቆምም፣
2
በእውነት፣ በቅንነትና በጽድቅ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብለህ ብትምል፣ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤ በእርሱም ይከበራሉ።”
3
እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላል፤ “ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤ በእሾኽም መካከል አትዝሩ።
4
እናንተ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፤ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤ አለዚያ ስለ ሠራችሁት ክፋት፣ ቍጣዬ እንደ እሳት ይንበለበላል፤ ሊገታውም የሚችል የለም።
5
“ ‘በምድሪቱ ሁሉ መለከትን ንፉ’ ብላችሁ፤ በይሁዳ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌም ዐውጁ፤ ጩኹ፤ እንዲህም በሉ፤ ‘በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ!’
6
ወደ ጽዮን ለመግባት ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ቶሎ ሸሽታችሁ አምልጡ፤ ከሰሜን መቅሠፍትን፣ ታላቅ ጥፋትን አመጣለሁና።”
7
አንበሳ ከደኑ ወጥቷል፤ ሕዝብንም የሚያጠፋ ተሰማርቷል፤ ምድርሽን ባዶ ሊያደርግ፣ ከስፍራው ወጥቷል። ከተሞችሽ ፈራርሰው ይወድቃሉ፤ ያለ ነዋሪም ይቀራሉ።
8
ስለዚህ ማቅ ልበሱ፤ ዕዘኑ፤ ዋይ በሉ፤ የእግዚአብሔር አስፈሪ ቍጣ፣ ከእኛ አልተመለሰምና።
9
“በዚያ ቀን” ይላል እግዚአብሔር ፤ “ንጉሡና ሹማምቱ ወኔ ይከዳቸዋል፤ ካህናቱ ድንጋጤ ይውጣቸዋል፤ ነቢያቱም ብርክ ይይዛቸዋል።”
10
እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰይፍ ዐንገታቸው ላይ ተቃጥቶ ሳለ፣ ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን ለምን እጅግ አታለልህ?” አልሁ።
11
በዚያን ጊዜ፣ ለእዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ “ለማበጠር ወይም ለማጥራት ሳይሆን፣ ከዚያ የበረታ የሚጠብስ ደረቅ ነፋስ በምድረ በዳ ካሉት ባድማ ኰረብቶች ወደ ወገኔ ሴት ልጅ
12
በእኔ ትእዛዝ ይነፍሳል፤ እንግዲህ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።”
13
እነሆ፤ እንደ ደመና ይንሰራፋል፤ ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣሉ፤ ፈረሶቹም ከንስር ይፈጥናሉ፤ መጥፋታችን ነውና ወዮልን!
14
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እንድትድኚ ከልብሽ ክፋት ታጠቢ፤ እስከ መቼ ክፉ ሐሳብ በውስጥሽ ይኖራል?
15
ድምፅ ከዳን ይሰማልና፤ ከኤፍሬም ተራሮችም ጥፋትን ያውጃል።
16
“ይህን ለሕዝቦች አሳውቁ፤ ለኢየሩሳሌምም እንዲህ ብላችሁ በይፋ ንገሩ፤ ‘ከብበው የሚያስጨንቁ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይደነፋሉ፤
17
ሰብል እንደሚጠብቁ ሰዎች ይከቧታል፤ በእኔ ላይ ዐምፃለችና፤’ ” ይላል እግዚአብሔር ።
18
“የገዛ መንገድሽና ተግባርሽ፣ ይህን አምጥቶብሻል፤ ይህም ቅጣትሽ ነው፤ ምንኛ ይመርራል! እንዴትስ ልብ ይሰብራል!”
19
ወይ አበሳዬ! ወይ አበሳዬ! ሥቃይ በሥቃይ ላይ ሆነብኝ፤ አወይ፣ የልቤ ጭንቀት! ልቤ ክፉኛ ይመታል፤ ዝም ማለት አልችልም፤ የመለከትን ድምፅ፣ የጦርነትንም ውካታ ሰምቻለሁና።
20
ጥፋት በጥፋት ላይ ይመጣል፤ ምድሪቱም በሞላ ባድማ ትሆናለች፤ ድንኳኔ በድንገት፣ መጠለያዬም በቅጽበት ጠፋ።
21
እስከ መቼ የጦርነት ዐርማ እመለከታለሁ? እስከ መቼስ የመለከት ድምፅ እሰማለሁ?
22
“ሕዝቤ ተላሎች ናቸው፤ እኔን አያውቁኝም። ማስተዋል የጐደላቸው፣ መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው። ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፣ መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።”
23
ምድርን ተመለከትሁ፤ እነሆ ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች፤ ሰማያትንም አየሁ፣ ብርሃናቸው ጠፍቷል።
24
ተራሮችን ተመለከትሁ፣ እነሆ ይንቀጠቀጡ ነበር፤ ኰረብቶችም ሁሉ ተናጡ።
25
አየሁ፤ ሰው አልነበረም፤ የሰማይ ወፎች ሁሉ በረው ጠፍተዋል።
26
ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ፍሬያማው ምድር በረሓ ሆነ፤ ከተሞቹ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት፣ ከብርቱ ቍጣው የተነሣ ፈራረሱ።
27
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፤ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም።
28
ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማያትም በላይ ይጨልማሉ፤ ተናግሬአለሁ፤ ሐሳቤን አልለውጥም፤ ወስኛለሁ፤ ወደ ኋላም አልልም።”
29
ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጩኸት የተነሣ፣ ከተማ ሁሉ ይሸሻል፤ አንዳንዶች ደን ውስጥ ይገባሉ፤ ሌሎችም ቋጥኝ ላይ ይወጣሉ፤ ከተሞች ሁሉ ባዶ ቀርተዋል፤ የሚኖርባቸውም የለም።
30
አንቺ ለጥፋት የተዳረግሽ ሆይ፤ ምን መሆንሽ ነው? ቀይ ቀሚስ የለበስሽው ለምንድን ነው? ለምን በወርቅ አጌጥሽ? ዐይኖችሽንስ ለምን ተኳልሽ? እንዲያው በከንቱ ተሽሞንሙነሻል፤ የተወዳጀሻቸው ንቀውሻልና፤ ነፍስሽንም ሊያጠፉ ይፈልጋሉ።
31
የበኵር ልጇን ለመውለድ እንደምታምጥ፣ በወሊድ እንደምትጨነቅ ሴት ድምፅ ሰማሁ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ትንፋሽ ዐጥሯት ስትጮኽ፣ እጇን ዘርግታ፣ “ወዮልኝ! ተዝለፈለፍሁ፣ በነፍሰ ገዳዮች እጅ ወደቅሁ!” ስትል ሰማሁ።
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 51
Chapter 52
Chapter 5 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52