bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Jonah 2
Jonah 2
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 3 →
1
ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤
2
እንዲህም አለ፤ “ተጨንቄ ሳለሁ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከመቃብሩም ጥልቅ ርዳታን ፈልጌ ተጣራሁ፤ አንተም ጩኸቴን ሰማህ።
3
ጥልቅ ወደ ሆነው፣ ወደ ባሕሩ መካከል ጣልኸኝ፤ ፈሳሾችም ዙሪያዬን ከበቡኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣ በላዬ ዐለፉ።
4
እኔም፣ ‘ከፊትህ ጠፋሁ፣ ነገር ግን እንደ ገና፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ፣ እመለከታለሁ’ አልሁ።
5
ውሃ እስከ ዐንገቴ አጠለቀኝ ፤ ጥልቁም ከበበኝ፤ የባሕርም ዐረም በራሴ ላይ ተጠመጠመ።
6
ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ፤ የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ግን ሕይወቴን ከጕድጓድ አወጣህ።
7
“ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች።
8
“ከንቱ በሆኑ ጣዖቶች ላይ የሚንጠለጠሉ፣ ሊያገኙ የሚገባቸውን ጸጋ ያጣሉ።
9
እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤ ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።”
10
እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፤ ዮናስንም በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4