bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Joshua 12
Joshua 12
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 11
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 13 →
1
እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ ማዶ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን የዓረባን ክፍል በሙሉ ይዞ፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ የሚዘልቀውን ግዛታቸውን የወሰዱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤
2
መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፣ ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ላይ ካለችው ከአሮዔር ማለት ከሸለቆው መካከል አንሥቶ፣ የአሞናውያን ወሰን እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ገዝቷል፤ ይህም የገለዓድን እኩሌታ ይጨምራል።
3
እንዲሁም ከኪኔሬት ባሕር እስከ ሙት ባሕር ያለውን ምሥራቃዊውን ዓረባ፣ እስከ ቤት የሺሞትና ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ ፈስጋ ተራራ ግርጌ ድረስ ገዝቷል።
4
መቀመጫውን በአስታሮትና በኤድራይ አድርጎ የገዛውና ከመጨረሻዎቹ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነው የባሳን ንጉሥ ዐግ፣
5
የአርሞንዔምን ተራራ፣ ሰልካንን፣ ባሳንን ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ድንበሮች እንዲሁም ከገለዓድ እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ወሰን ድረስ ገዝቷል።
6
የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ድል አደረጉ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴም ምድራቸውን ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
7
እንግዲህ ኢያሱና እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ድል ያደረጓቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ ካለው ከበኣልጋድ ተነሥቶ በምዕራብ ሴይር እስካለው እስከ ሐላቅ ተራራ ይደርሳል፤ ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ምድር እንደ ነገዳቸው አከፋፈል ለእስራኤላውያን በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
8
ይህም ተራራማው አገር፤ በስተ ምዕራብ ያለው የኰረብታ ግርጌ፣ ዓረባ፣ የተራራው ሸንተረሮች፣ ምድረ በዳውና ነጌብ ማለት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው፤ ነገሥታቱም እነዚህ ናቸው፤
9
የኢያሪኮ ንጉሥ፣ አንድ፤ ቤቴል አጠገብ ያለችው የጋይ ንጉሥ፣ አንድ፤
10
የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ አንድ፤ የኬብሮን ንጉሥ፣ አንድ፤
11
የየርሙት ንጉሥ፣ አንድ፤ የለኪሶ ንጉሥ፣ አንድ፤
12
የዔግሎን ንጉሥ፣ አንድ፤ የጌዝር ንጉሥ፣ አንድ፤
13
የዳቤር ንጉሥ፣ አንድ፤ የጌድር ንጉሥ፣ አንድ፤
14
የሔርማ ንጉሥ፣ አንድ፤ የዓራድ ንጉሥ፣ አንድ፤
15
የልብና ንጉሥ፣ አንድ፤ የዓዶላም ንጉሥ፣ አንድ፤
16
የመቄዳ ንጉሥ፤ አንድ፤ የቤቴል ንጉሥ፣ አንድ፤
17
የታጱዋ ንጉሥ፣ አንድ፤ የኦፌር ንጉሥ፣ አንድ፤
18
የአፌቅ ንጉሥ፣ አንድ፤ የለሸሮን ንጉሥ፣ አንድ፤
19
የማዶን ንጉሥ፣ አንድ፤ የሐጾር ንጉሥ፣ አንድ፤
20
የሺምሮን ሚሮን ንጉሥ፣ አንድ፤ የአዚፍ ንጉሥ፣ አንድ፤
21
የታዕናክ ንጉሥ፣ አንድ፤ የመጊዶ ንጉሥ፣ አንድ፤
22
የቃዴስ ንጉሥ፣ አንድ፤ በቀርሜሎስ የሚገኘው የዮቅንዓም ንጉሥ፣ አንድ፤
23
በዶር ኰረብታ የሚገኘው የዶር ንጉሥ፣ አንድ፤ በጌልገላ የሚገኘው የጎይም ንጉሥ፣ አንድ፤
24
የቲርሳ ንጉሥ፣ አንድ። እነዚህ በድምሩ ሠላሳ አንድ ነገሥታት ናቸው።
← Chapter 11
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 13 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24