bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Nahum 1
Nahum 1
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 2 →
1
ስለ ነነዌ ጥፋት የተነገረ ንግር፤ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፤
2
እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር የሚበቀል፣ በመዓትም የተሞላ ነው። እግዚአብሔር ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ በጠላቶቹም ላይ ቍጣውን ያመጣል።
3
እግዚአብሔር ለቍጣ የዘገየ፣ በኀይሉም ታላቅ ነው፤ እግዚአብሔር በደለኛውን ሳይቀጣ አያልፍም፤ መንገዱ በዐውሎ ነፋስና በማዕበል ውስጥ ነው፤ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።
4
ባሕርን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል። ባሳንና ቀርሜሎስ ጠውልገዋል፤ የሊባኖስም አበቦች ረግፈዋል።
5
ተራሮች በፊቱ ታወኩ፤ ኰረብቶችም ቀለጡ። ምድር በፊቱ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖሩት ሁሉ ተናወጡ።
6
ቍጣውን ማን ሊቋቋም ይችላል? ጽኑ ቍጣውንስ ማን ሊሸከም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሷል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጥቀዋል።
7
እግዚአብሔር መልካም ነው፤ በጭንቅ ጊዜም መሸሸጊያ ነው። ለሚታመኑበት ይጠነቀቅላቸዋል፤
8
ነነዌን ግን፣ በሚያጥለቀልቅ ጐርፍ ያጠፋታል፤ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።
9
በእግዚአብሔር ላይ ምንም ቢያሤሩ ፣ እርሱ ያጠፋዋል፤ መከራም ዳግመኛ አይነሣም።
10
በእሾኽ ይጠላለፋሉ፤ በወይን ጠጃቸውም ይሰክራሉ፤ እሳትም እንደ ገለባ ይበላቸዋል።
11
ነነዌ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ላይ የሚያሤር፣ ክፋትንም የሚመክር፣ ከአንቺ ዘንድ ወጥቷል።
12
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምንም ኀይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑም፣ ይቈረጣሉ፤ ይጠፋሉም። ይሁዳ ሆይ፤ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ ከእንግዲህ አላስጨንቅህም።
13
አሁንም ቀንበራቸውን ከዐንገትህ ላይ አንሥቼ እሰብራለሁ፤ የታሰርህበትንም ሰንሰለት በጥሼ እጥላለሁ።”
14
አንቺ ነነዌ፤ እግዚአብሔር ስለ አንቺ እንዲህ ብሎ አዝዟል፤ “ስም የሚያስጠራ ትውልድ አይኖራችሁም፤ በአማልክታችሁ ቤት ያሉትን፣ የተቀረጹትን ምስሎችና ቀልጠው የተሠሩትን ጣዖታት እደመስሳለሁ፤ መቀበሪያህን እምስልሃለሁ፤ አንተ ክፉ ነህና።”
15
እነሆ፤ የምሥራች የሚያመጣው፣ ሰላምን የሚያውጀው ሰው እግር፣ በተራሮች ላይ ነው፤ ይሁዳ ሆይ፤ በዓላትህን አክብር፤ ስእለትህንም ፈጽም፤ ከእንግዲህ ክፉዎች አይወርሩህም፤ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 2 →
All chapters:
1
2
3