bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Numbers 25
Numbers 25
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 24
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 26 →
1
እስራኤላውያን በሰጢም በነበሩበት ጊዜ ወንዶቹ ከሞዓብ ሴቶች ጋር ማመንዘር ጀመሩ።
2
እነዚህም ሴቶች ወደ አምላኮቻቸው መሥዋዕት ሕዝቡን ጋበዙ፤ ሕዝቡም መሥዋዕቱን በላ፤ ለአማልክቱም ሰገደ።
3
ስለዚህ እስራኤል የፌጎርን በኣል በማምለክ ተባበረ፤ የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ቍጣ በላዩ ነደደ።
4
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “አስፈሪው የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቍጣ ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ ግደልና በጠራራ ፀሓይ ላይ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ስቀላቸው” አለው።
5
ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፣ “እያንዳንዳችሁ የፌጎርን በኣል በማምለክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው።”
6
ከዚህ በኋላ ሙሴና መላው የእስራኤል ማኅበር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ እያለቀሱ ሳለ፣ አንድ እስራኤላዊ እነርሱ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት ይዞ ወደ ቤተ ሰቡ መጣ።
7
የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ይህን ባየ ጊዜ ማኅበሩን ትቶ ጦሩን በእጁ በመያዝ፣
8
እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ፤ ጦሩንም ወርውሮ እስራኤላዊውንና ሴቲቱን አጣምሮ ወጋቸው። ከዚያም በእስራኤላውያን ላይ የወረደው መቅሠፍት ተከለከለ፤
9
ሆኖም በመቅሠፍቱ የሞተው ሰው ቍጥር ሃያ አራት ሺሕ ደርሶ ነበር።
10
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
11
“የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ እኔ ለክብሬ በመካከላቸው እንደምቀና ስለ ቀና ቍጣዬን ከእስራኤላውያን መልሶታል፤ ስለዚህ እኔም በቅናቴ ጨርሶ አላጠፋኋቸውም፤
12
ስለዚህ እነሆ እኔ የሰላም ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር እንደማደርግ ንገረው።
13
ለአምላኩ (ኤሎሂም) ክብር ቀንቶ ለእስራኤላውያን ስላስተሰረየላቸው፣ እርሱና ልጆቹ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል።”
14
ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው እስራኤላዊ የሰሉ ልጅ ዘንበሪ ይባላል፤ የስምዖናውያን ቤተ ሰብ አለቃ ነበር።
15
እንዲሁም የተገደለችዋ ምድያማዊት ሴት ከስቢ ትባላለች፤ እርሷም ከምድያማውያን ቤተ ሰብ የአንዱ ነገድ አለቃ የሆነው የሱር ልጅ ነበረች።
16
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
17
“ምድያማውያንን እንደ ጠላት ቈጥራችሁ ፍጇቸው።
18
ይኸውም ፌጎር ላይ በተፈጸመው ድርጊትና በፌጎር ምክንያት በመጣው መቅሠፍት በተገደለችው በምድያማዊው አለቃ ልጅ፣ በእኅታቸው በከስቢ አታልለው የጠላትነት ሥራ ስለ ሠሩባችሁ ነው።”
← Chapter 24
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 26 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36