bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Proverbs 19
Proverbs 19
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 18
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 20 →
1
ንግግሩ ጠማማ ከሆነ ዐጕል ሰው ይልቅ፣ ያለ ነውር የሚሄድ ድኻ ሰው ይሻላል።
2
ዕውቀት አልባ የሆነ ቀናኢነት መልካም አይደለም፤ ጥድፊያም መንገድን ያስታል።
3
ሰው በራሱ ተላላነት ሕይወቱን ያበላሻል፤ በልቡ ግን እግዚአብሔርን ያማርራል።
4
ሀብት ብዙ ወዳጅ ታፈራለች፤ ድኻን ግን ወዳጁ ገሸሽ ያደርገዋል።
5
ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ ውሸት የሚነዛም ሳይቀጣ አይቀርም።
6
ብዙ ሰዎች በገዥ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያሸረግዳሉ፤ ስጦታን ከሚሰጥ ሰው ጋር ሁሉም ወዳጅ ነው።
7
ድኻ በሥጋ ዘመዶቹ ሁሉ የተጠላ ነው፤ ታዲያ ወዳጆቹማ የቱን ያህል ይሸሹት! እየተከታተለ ቢለማመጣቸውም፣ ከቶ አያገኛቸውም።
8
ጥበብን ገንዘቡ የሚያደርጋት ነፍሱን ይወድዳል፤ ማስተዋልን የሚወድዳት ይሳካለታል።
9
ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ ውሸት የሚነዛም ይጠፋል።
10
ተላላ ተንደላቅቆ መኖር አይገባውም፤ ባሪያ የመሳፍንት ገዥ ከሆነማ የቱን ያህል ይከፋ!
11
ጥበብ ሰውን ታጋሽ ታደርገዋለች፤ በደልን ንቆ መተውም መከበሪያው ነው።
12
የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤ በፊቱ ሞገስ ማግኘትም በሣር ላይ እንዳለ ጠል ነው።
13
ተላላ ልጅ ለአባቱ መጥፊያ ነው፤ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት።
14
ቤትና ሀብት ከወላጆች ይወረሳሉ፤ አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት።
15
ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ ዋልጌም ሰው ይራባል።
16
ትእዛዞችን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፤ መንገዱን የሚንቅ ግን ይሞታል።
17
ለድኻ የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ ስላደረገውም ተግባር ዋጋ ይከፍለዋል።
18
ገና ተስፋ ሳለ፣ ልጅህን ሥርዐት አስይዘው፤ ሲሞት ዝም ብለህ አትየው።
19
ግልፍተኛ ሰው ቅጣትን መቀበል ይገባዋል፤ በምሕረት ካለፍኸው ሌላም ጊዜ አይቀርልህም።
20
ምክርን ስማ፤ ተግሣጽን ተቀበል፤ በመጨረሻም ጠቢብ ትሆናለህ።
21
በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው።
22
ሰው የሚመኘው ጽኑ ፍቅር ነው፤ ውሸታም ከመሆንም ድኻ መሆን ይሻላል።
23
እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤ እንዲህ ያለውም ሰው እፎይ ብሎ ያርፋል፤ መከራም አያገኘውም።
24
ሰነፍ እጁን ከወጭቱ ያጠልቃል፤ ወደ አፉ ግን መመለስ እንኳ ይሳነዋል።
25
ፌዘኛን ግረፈው፤ ብስለት የሌለውም ማስተዋልን ይማራል፤ አስተዋይን ዝለፈው፤ ዕውቀትን ይገበያል።
26
አባቱን የሚዘርፍ፣ እናቱንም የሚያሳድድ፣ ዕፍረትና ውርደት የሚያመጣ ልጅ ነው።
27
ልጄ ሆይ፤ እስቲ ምክርን ማዳመጥ ተው፤ ከዕውቀትም ቃል ትስታለህ።
28
አባይ ምስክር በፍትሕ ላይ ያፌዛል፤ የክፉዎችም አፍ በደልን ይሰለቅጣል።
29
ለፌዘኞች ቅጣት፣ ለተላሎችም ጀርባ ጅራፍ ተዘጋጅቷል።
← Chapter 18
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 20 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31