bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Song of Solomon 3
Song of Solomon 3
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 4 →
1
ሌሊቱን ሙሉ በዐልጋዬ ላይ ሆኜ፣ ውዴን ተመኘሁ፤ ተመኘሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።
2
ተነሥቼ ወደ ከተማዪቱ እወጣለሁ፤ በዋና ዋና መንገዶችና በአደባባዮች እዘዋወራለሁ፤ ውዴንም እፈልገዋለሁ፤ ስለዚህም ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።
3
በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣ የከተማዪቱ ጠባቂዎች አገኙኝ፤ እኔም፣ “ውዴን አይታችኋል?” አልኋቸው።
4
ከእነርሱ ጥቂት ዕልፍ እንዳልሁ፣ ውዴን አገኘሁት፤ ያዝሁት፤ ወደ እናቴ ቤት እስካመጣው፣ በማሕፀን ወደ ተሸከመችኝም ዕልፍኝ እስካገባው ድረስ አልለቀውም።
5
እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣ በሚዳቋና በሜዳ ዋሊያ አማጥናችኋለሁ።
6
ከከርቤና ከዕጣን፣ ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣ መዐዛዋ የሚያውድ፣ እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትወጣው ይህች ማን ናት?
7
እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላ በታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣ ስድሳ ጦረኞች ታጅባለች፤
8
ሁሉም ሰይፍ የታጠቁ፣ ሁሉም በጦርነት የተፈተኑ ናቸው፤ የሌሊት አደጋን ለመከላከልም፣ እያንዳንዳቸው ሰይፋቸውን በወገባቸው ታጥቀዋል።
9
ንጉሥ ሰሎሞን የራሱን ሠረገላ ሠራ፤ የሠራውም ከሊባኖስ በመጣ ዕንጨት ነው።
10
ምሰሶዎቹን ከብር፣ መደገፊያውንም ከወርቅ ሠራ፤ መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ ውስጡም በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ አምሮ የተለበጠ ነው።
11
እናንት የጽዮን ቈነጃጅት ውጡ፤ ንጉሥ ሰሎሞን አክሊሉን ደፍቶ እዩት፤ ዘውዱም ልቡ ሐሤት ባደረገባት፣ በዚያች በሰርጉ ዕለት፣ እናቱ የደፋችለት ነው።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8