bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Zechariah 4
Zechariah 4
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 5 →
1
ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ተመልሶ፣ አንድ ሰው ከእንቅልፉ እንደሚነቃ አነቃኝ፤
2
እርሱም፣ “ምን ታያለህ?” አለኝ። እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ በዐናቱ ላይ የዘይት ማሰሮ ያለበት ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ አየሁ፤ በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ።
3
ደግሞም አንዱ ከዘይቱ ማሰሮ በስተ ቀኝ፣ ሌላውም በስተ ግራ የሆኑ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”
4
ያነጋግረኝ የነበረውንም መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እነዚህ ምንድን ናቸው” አልሁት።
5
እርሱም፣ “ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።
6
ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለዘሩባቤል የተላከው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ‘በመንፈሴ እንጂ በኀይልና በብርታት አይደለም’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።
7
“ታላቅ ተራራ ሆይ፤ አንተ ምንድን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎች፣ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ፣ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።”
8
ደግሞም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤
9
“የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤተ መቅደስ መሠረት ጣሉ፤ የሚፈጽሙትም የእርሱ እጆች ናቸው። ከዚያም እግዚአብሔር ጸባኦት እኔን ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
10
“የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱ በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”
11
ከዚያም መልአኩን፣ “ከመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉት እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።
12
እንደ ገናም፣ “በሁለቱ የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈስሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅርንጫፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።
13
እርሱም፣ “ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።
14
እርሱም፣ “እነዚህ ሁለቱ የምድርን ሁሉ ጌታ ለማገልገል የተቀቡ ናቸው” አለኝ።
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 5 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14