bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
2 Chronicles 1
2 Chronicles 1
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 2 →
1
የዳዊት ልጅ ንጉሥ ሰሎሞን መንግሥቱን አጠናከረ፤ እግዚአብሔር አምላኩም ባረከው፤ እጅግ በጣም ገናናም አደረገው።
2
ንጉሥ ሰሎሞን ለእስራኤላውያን ሁሉ፥ ለሺህ አለቆችና ለመቶ አለቆች፥ እንዲሁም ለመንግሥቱ ባለ ሥልጣኖች፥ ለቤተሰብ መሪዎችና ሕዝብ በሙሉ፥
3
በገባዖን ወደሚገኘው ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራ አብረውት እንዲሄዱ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወደዚያ የሄዱበትም ምክንያት፥ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው፥ እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን በዚያው በገባዖን ስለሚገኝ ነው።
4
የቃል ኪዳኑ ታቦት ግን ንጉሥ ዳዊት ከቂርያትይዓሪም ባመጣው ጊዜ በኢየሩሳሌም አዘጋጅቶለት በነበረው ድንኳን ውስጥ ይገኝ ነበር።
5
የሑር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባጽልኤል ከነሐስ የሠራው መሠዊያም በዚያው በገባዖን በድንኳኑ ፊት ለፊት ነበረ፤ በዚያም ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤
6
ንጉሡም እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን ፊት ለፊት ባለው ከነሐስ በተሠራው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት በማቅረብ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ አንድ ሺህ እንስሶችንም አሳርዶ በመሠዊያው ላይ እንዲቃጠሉ አደረገ።
7
በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ለሰሎሞን ተገልጦ “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” ሲል ጠየቀው።
8
ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንተ ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ ፍቅርህን ባለማቋረጥ አሳይተኸዋል፤ አሁንም እኔ በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ አድርገሃል፤
9
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ለአባቴ የሰጠኸው የተስፋ ቃል እንዲፈጸም አድርግ፤ እነሆ ከብዛቱ የተነሣ ሊቈጠር በማይችል ሕዝብ ላይ አንግሠኸኛል፤
10
ስለዚህ ሕዝብህን በትክክል ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብና ዕውቀት ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሕዝብህን እንዴት ልመራ እችላለሁ?”
11
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ለራስህ ባለጸግነትን ወይም ሀብትን፥ ዝናን ወይም የጠላቶችህን ሞት፥ ወይም ረጅም ዕድሜን ሳይሆን በእነርሱ ላይ እንድትነግሥ ያደረግኩህን ሕዝቤን በትክክል ለመምራት የሚያስችልህን ጥበብና ዕውቀት በመጠየቅህ፥
12
ስለዚህ እነሆ የጠየቅኸውን ጥበብና ዕውቀት እሰጥሃለሁ፤ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ማንም ንጉሥ ካገኘውና ወደፊትም ማንም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ብልጽግና፥ ሀብትና ዝና እሰጥሃለሁ።”
13
ሰሎሞን እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን ካለበት፥ በገባዖን ከሚገኘው ኰረብታማ ማምለኪያ ስፍራ ተነሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ በእስራኤል ላይ ነገሠ።
14
ሰሎሞን በአንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና በዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች የተጠናከረ ሠራዊትን አደራጀ፤ ከእነርሱም ከፊሉን በኢየሩሳሌም፥ የቀረውን ደግሞ በሌሎች ልዩ ልዩ ከተሞች በመመደብ በዚያው እንዲኖሩ አደረገ።
15
በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በኢየሩሳሌም ወርቅና ብር ከመብዛቱ የተነሣ እንደ ድንጋይ ተራ ነገር ነበር፤ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅል ሾላ ዛፍ ይቈጠር ነበር።
16
የንጉሡም ፈረሶች የሚመጡት፥ ከግብጽና ከቀዌ ነበር፤ የንጉሡም ነጋዴዎች ከቀዌ ይገዙአቸው ነበር።
17
ከግብጽ ለሚገዛው ለያንዳንዱ ሠረገላ ስድስት መቶ ጥሬ ብር ለያንዳንዱ ፈረስ አንድ መቶ ኀምሳ ጥሬ ብር ይከፍሉ ነበር። እነርሱም መልሰው ለሒታውያንና ለሶርያ ነገሥታት ይሸጡላቸው ነበር።
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 2 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36