bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
3 John 1
3 John 1
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
Jump to:
Chapter 1
1
በእውነት ለማፈቅረው፥ ለተወደደው ጋይዮስ፥ ከእኔ ከሽማግሌው የተላከ መልእክት፦
2
ወዳጄ ሆይ! ኑሮህ ሁሉ እንዲሳካልህ፥ ጤንነት እንዲኖርህና እንዲሁም የመንፈስ እርካታ እንድታገኝ እመኝልሃለሁ።
3
ለእውነት ታማኝነትህንና በእውነትም መኖርህን አንዳንድ ክርስቲያን ወንድሞች መጥተው በነገሩኝ ጊዜ በጣም ደስ ተሰኘሁ።
4
ልጆቼ በእውነት እየተመላለሱ መኖራቸውን ከመስማት የበለጠ የሚያስደስተኝ ነገር የለም።
5
ወዳጄ ሆይ! ለአንተ እንግዶች ቢሆኑም እንኳ ለወንድሞች ታማኝ አገልግሎት ትሰጣለህ።
6
እነርሱም ስለ አደረግህላቸው የፍቅር ሥራ በማኅበረ ምእመናን ፊት መስክረዋል፤ አሁንም እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ በጒዞአቸው ብትረዳቸው መልካም ነው።
7
እነርሱ ክርስቶስን ለማገልገል ሲወጡ ከአሕዛብ ምንም ርዳታ አልተቀበሉም።
8
የእውነት ሥራ ተካፋዮች እንድንሆን እንደእነዚህ ያሉትን ሰዎች መርዳት አለብን።
9
ከዚህ በፊት ለቤተ ክርስቲያን ደብዳቤ ጽፌአለሁ፤ ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን መሪ መሆን የሚፈልገው ዲዮትሬፊስ አሳቤን አልተቀበለም።
10
ስለዚህ ወደ እናንተ ስመጣ እርሱ እየሰደበንና እያዋረደን ያደረገውን ክፉ ሥራ ሁሉ ለሁሉም እናገራለሁ፤ ይህም ሳይበቃው ቀርቶ፤ እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም። ሌሎችም እንዳይቀበሉአቸው ይከለክላል። ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።
11
ወዳጄ ሆይ! ደጉን ምሰል እንጂ ክፉውን አትምሰል። ደግ ሥራ የሚሠራ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው። ክፉ ሥራ የሚሠራ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።
12
ለድሜጥሮስ ሰው ሁሉ በመልካም ይመሰክርለታል። እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች። እኛም እንመሰክርለታለን፤ የእኛም ምስክርነት እውነት መሆኑን ታውቃለህ።
13
ልጽፍልህ የምፈልገው ብዙ ነገር ነበረኝ፤ ነገር ግን በደብዳቤ ልገልጽልህ አልፈልግም።
14
በቅርቡ ላይህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በዚያን ጊዜ ቃል በቃል እንነጋገራለን።
15
ሰላም ለአንተ ይሁን። ወዳጆች ሰላምታ ያቀርቡልሃል። አንተም ለወዳጆቻችን አንድ በአንድ ሰላምታ አቅርብልን።
Jump to:
Chapter 1
All chapters:
1