bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Colossians 3
Colossians 3
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 4 →
1
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከሞት ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ በሰማይ ያሉትን ነገሮች ፈልጉ።
2
ዘወትር በላይ በሰማይ ስላሉት ነገሮች አስቡ እንጂ በምድር ላይ ስላሉት ነገሮች አታስቡ።
3
እናንተ በሞት የመለየትን ያኽል ከዚህ ዓለም ተለይታችኋል፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ተሰውሮአል።
4
ሕይወታችሁ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።
5
ስለዚህ በእናንተ የሚገኙትን የምድራዊ ሕይወት ምኞቶች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም “ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ፍትወት፥ ክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማምለክ የሆነ መጐምጀት” ናቸው።
6
በእነዚህ ነገሮች ምክንያት በማይታዘዙ ሰዎች ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ ይመጣል።
7
እናንተም ራሳችሁ ከዚህ በፊት በማይታዘዙ ሰዎች መካከል ሳላችሁ እነዚህን ነገሮች በማድረግ ትኖሩ ነበር።
8
አሁን ግን ቊጣን፥ ንዴትን፥ ተንኰልን፥ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።
9
አሮጌውን ባሕርይ ከነሥራው አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁት እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ።
10
በፈጣሪው አምሳል በዕውቀት እየታደሰ የሚሄደውን አዲሱን ባሕርይ ልበሱ።
11
በዚህ ሁኔታ በግሪካዊና በአይሁዳዊ፥ በተገረዘና ባልተገረዘ፥ በሠለጠነ አረመኔና ባልሠለጠነ አረመኔ፥ ነጻነት በሌለውና ነጻነት ባለው ሰው መካከል ልዩነት የለም፤ ክርስቶስ ሁሉም ነው፤ በሁሉም ነው።
12
እንግዲህ የእግዚአብሔር ምርጦችና ቅዱሳን፥ የተወደዳችሁም እንደ መሆናችሁ መጠን ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ ገርነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ።
13
እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ይቅር በሉ።
14
ከዚህም ሁሉ በላይ ሁሉን ነገር ሰብስቦ በማሰር ፍጹም አንድነትን የሚያስገኘውን ፍቅርን ልበሱ።
15
የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ በእርግጥ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
16
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
17
በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት፤ በእርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑ።
18
ሚስቶች ሆይ! በጌታ ዘንድ ተገቢ ስለ ሆነ ለባሎቻችሁ ታዘዙ።
19
ባሎች ሆይ! ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ ጨካኞችም አትሁኑባቸው።
20
ልጆች ሆይ! ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ ስለ ሆነ በሁሉ ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።
21
ወላጆች ሆይ! ተስፋ እንዳይቈርጡ ልጆቻችሁን በቊጣ አታበሳጩአቸው።
22
በባርነት ሥርዓት ያላችሁ! ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉም ነገር ታዘዙ፤ የምትታዘዙትም እነርሱ ስለሚያዩአችሁና ሰውን ደስ ስለምታሰኙ ለታይታ ሳይሆን ጌታን በመፍራትና በልብ ቅንነት ይሁን።
23
የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ ኢየሱስ እንደምታደርጉት ዐይነት ከልባችሁ አድርጉት።
24
ለዚህም ጌታ ሰማያዊ ርስትን ዋጋ አድርጎ እንደሚሰጣችሁ ታውቃላችሁ፤ የምታገለግሉትም ጌታ ክርስቶስን ነው፤
25
በእግዚአብሔር ዘንድ አድልዎ ስለሌለ ክፉ የሚሠራም ስለ ክፉ ሥራው ቅጣቱን ይቀበላል።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4