bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Ecclesiastes 1
Ecclesiastes 1
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 2 →
1
በኢየሩሳሌም ነግሦ የነበረ ጥበበኛው የዳዊት ልጅ የተናገረው የጥበብ ቃል ይህ ነው፤
2
ጥበበኛው እንዲህ አለ፦ ሁሉ ነገር ከንቱ፥ እንዲያውም የከንቱ ከንቱ ነው፤ ሁሉም ነገር በፍጹም ከንቱ ነው።
3
ሰው በሚኖርበት ዓለም በሥራ የሚደክምበት ነገር ሁሉ ትርፉ ምንድን ነው?
4
ትውልድ አልፎ ትውልድ ይተካል፤ ምድር ግን ሳትለወጥ ለዘለዓለሙ ጸንታ ትኖራለች።
5
ፀሐይ ወጥታ ትጠልቃለች፤ እንደገናም ወደምትወጣበት ስፍራ ለመድረስ ትጣደፋለች።
6
ነፋስ ወደ ደቡብም፥ ወደ ሰሜንም ይነፍሳል፤ ዞሮ ዞሮም እንደገና ይመለሳል።
7
የወንዝ ውሃ ሁሉ ወደ ባሕር ይፈስሳል፤ ባሕሩ ግን አይሞላም፤ ውሃ ተመልሶ እንደገና ወደሚፈልቅበት ወደ ወንዞቹ መነሻ ይሄዳል።
8
ሁሉ ነገር አሰልቺ ነው፤ አሰልቺነቱንም ሰው በቃል ገልጦ ሊናገረው እንኳ አይችልም፤ ዐይን አይቶ አይጠግብም፤ ጆሮም ሰምቶ በቃኝ አይልም።
9
ቀድሞ የሆነው ነገር እንደገና ይሆናል፤ አሁንም የሚደረገው ነገር ሁሉ ያው ቀድሞ የተደረገው ነው፤ ስለዚህ በመላው ዓለም አዲስ ተብሎ የሚጠራ ምንም ነገር የለም።
10
ማንም ሰው “እነሆ ይህ አዲስ ነገር ነው!” ቢል ያ ነገር እኛ ከመወለዳችን አስቀድሞ የነበረ ሆኖ ይገኛል።
11
ባለፉት ዘመናት ተደርገው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ የሚያስታውስ የለም፤ ከእነርሱም በኋላ ተከታትለው የሚመጡትም ነገሮች ቢሆኑ በተተኪው ትውልድ ዘንድ መታሰቢያ አይኖራቸውም።
12
እኔ ተናጋሪው በኢየሩሳሌም የእስራኤል ንጉሥ ነበርኩ፤
13
ታዲያ፥ በዚህ ዓለም የተደረጉትን ነገሮች ሁሉ በጥበብ መርምሬ ለማጥናት ወሰንኩ፤ ይህችን ከባድ ጭነት የሰው ልጆች ይደክሙበት ዘንድ እግዚአብሔር ሰጥቶአቸዋል።
14
እነሆ በዚህ ዓለም ላይ የተደረገውን ነገር ሁሉ ተመለከትኩ፤ ይሁን እንጂ ሁሉ ነገር ከንቱ ሆኖ አገኘሁት፤ ሁሉም ነገር ነፋስን እንደ መጨበጥ ሆኖ ይቈጠራል።
15
ጠማማው ሊቀና አይችልም፤ የሌለ ነገር ሊቈጠር አይቻልም።
16
እኔማ በልቤ “ከእኔ በፊት ኢየሩሳሌምን ከገዙት ሁሉ ይበልጥ ታላቅና የጥበብ ሰው ሆኛለሁ፤ የጥበብንና የዕውቀትን ምንነት መርምሬ አጥንቻለሁ” ብዬ ነበር፤
17
ስለዚህ ጥበብንና ዕውቀትን፥ እብደትንና ሞኝነትን ዐውቅ ዘንድ ኅሊናዬን አተጋለሁ፤ ይህም ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ሆኖ አገኘሁት።
18
ጥበብ በበዛ መጠን ትካዜ ይበዛል፤ ዕውቀትም በበዛ መጠን ጭንቀትን ያስከትላል።
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 2 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12