bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Habakkuk 1
Habakkuk 1
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 2 →
1
እግዚአብሔር ለነቢዩ ለዕንባቆም በራእይ የገለጠለት ቃል የሚከተለው ነው፦
2
እግዚአብሔር ሆይ! ርዳታህን በመጠየቅና በእኛ ላይ የደረሰውን ዐመፅ በመግለጥ ወደ አንተ ስንጮህ የምታዳምጠንና የምታድነን መቼ ነው?
3
ለምን ይህ ሁሉ ግፍ ሲደርስ እንዳይ አደረግኸኝ? አንተስ ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታለህ? ጥፋትንና ዐመፅን አያለሁ፤ ጠብና ክርክርም ይነሣሉ።
4
በዚህ መሠረት ሕግ ላልቶአል፤ ፍትሕም ተዛብቶአል፤ ክፉዎች በደጋግ ሰዎች ላይ ከበባ አድርገዋል፤ ስለዚህ ፍርድ ተጣሟል።
5
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “በዙሪያችሁ ያሉትን ሕዝቦች እስቲ ተመልከቱ፤ በምታዩት ሁሉ እጅግ ተደነቁ፤ ማንም ሰው ቢነግራችሁ እንኳ ልታምኑ የማትችሉትን አስደናቂ ነገር በዘመናችሁ እሠራለሁ።
6
እነሆ እነዚያን ጨካኞችና ችኲሎች ባቢሎናውያንን አስነሣባችኋለሁ፤ እነርሱ የራሳቸው ያልሆነውን ምድር ሁሉ በጦር ኀይል ለመያዝ በየሀገሩ ይዞራሉ።
7
እነርሱ አስፈሪና አስደንጋጭ ናቸው፥ የራሳቸውን ክብር ማስጠበቂያ ሕግ ያወጣሉ።
8
“ፈረሶቻቸው ከነብር ይበልጥ ፈጣኖች፥ ከማታ ተኲላ ይልቅ አስፈሪዎች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም እየጋለቡ ከሩቅ ይመጣሉ፤ ነጥቀው ለመብላትም እንደ ንስር ይበራሉ።
9
“ሠራዊታቸው ሁሉ የዐመፅ ሥራ ለመፈጸም ይገሠግሣሉ፤ ፊታቸው ከወደ ምሥራቅ እንደሚመጣ ነፋስ ያቃጥላል፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ።
10
በነገሥታት ላይ ይሳለቃሉ፤ መሪዎቻቸውንም ይንቃሉ፤ በምሽጎቹ ሁሉ ላይ በመሳቅ ዐፈር ቈልለው ይይዙዋቸዋል።
11
ከዚህ በኋላ እንደ ነፋስ ጠራርገው ይሄዳሉ፤ እነዚህ ጒልበታቸውን እንደ አምላካቸው የሚቈጥሩ ሰዎች በደለኞች ናቸው።”
12
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንተ ከጥንት ጀምሮ የነበርክ ቅዱስ ነህ፤ አንተ ስለምትጠብቀን አንሞትም፥ እነርሱ ፍርድህን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መድበሃቸዋል፤ አምባችን ሆይ! እኛን እንዲቀጡ ለእነርሱ ሥልጣን ሰጥተሃቸዋል።
13
ዐይኖችህ እጅግ የጠሩ ስለ ሆኑ፥ ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ማየት አይስማማህም፤ ታዲያ እነዚህን ዐመፀኞችን እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታቸዋለህ? ክፉዎችስ ከእነርሱ ይበልጥ ደጋግ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠፉ ሲነሡ ስለምን ዝም ትላለህ?
14
ሰዎችን እንደ ባሕር ዓሣዎችና መሪ እንደሌላቸው በደረታቸው እየተሳቡ እንደሚሄዱ ፍጥረቶች የምታደርጋቸው ለምንድን ነው?
15
ዓሣ በመንጠቆ እንደሚያዝ ጠላት ሁሉንም ይይዛቸዋል፤ በመረብም እንደሚጐተት ይጐትታቸዋል፤ በማከማቻው ይሰበስባቸዋል፤ ይህን በማድረጉ በደስታ ይፈነጥዛል።
16
በምግብ ስለሚያበለጽጉትና በቅንጦት እንዲኖር ስለሚያደርጉት ለመረቡ መሥዋዕት ያቀርባል፤ ለማከማቻውም ዕጣን ያጥናል።
17
ታዲያ እርሱ መረቡን እያራገፈና ያለምሕረት ሕዝቦችን እየፈጀ መቀጠል አለበትን?
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 2 →
All chapters:
1
2
3