bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Haggai 2
Haggai 2
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
1
ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ ሰባተኛው ወር በገባ በሃያ አንደኛው ቀን በነቢዩ ሐጌ አማካይነት እግዚአብሔር ዳግመኛ ተናገረ፤
2
ጌታ ይሁዳ ገዢ ለሆነው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፥ ሊቀ ካህናት ለሆነው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱና ተርፎ ከስደት ለተመለሰው ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር አለው።
3
“የዚህ ቤተ መቅደስ የቀድሞ ክብሩ እንዴት እንደ ነበረ ያየ ሰው በእናንተ መካከል አለን? ዛሬስ እንዴት ሆኖ ታዩታላችሁ? ይህ በእናንተ ዘንድ እንደሌለ የሚቈጠር አይደለምን?
4
አሁን ግን ዘሩባቤል ሆይ! በርታ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ! በርታ፤ የሀገሪቱ ሕዝብ ሆይ! በርቱ! እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ። እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ።
5
ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ ‘እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ’ ብዬ በሰጠሁት የተስፋ ቃል መሠረት አሁንም መንፈሴ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነ አይዞአችሁ አትፍሩ” ብሎ ነገራቸው።
6
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደገና ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንና የብስን አናውጣለሁ፤
7
መንግሥታትን ሁሉ እገለብጣለሁ፤ ሀብታቸውንም ሁሉ ወደዚህ እንዲመጣ አደርጋለሁ፤ ስለዚህም ቤተ መቅደሱ በሀብት የተሞላ ይሆናል።
8
በዓለም የሚገኝ ወርቅና ብር ሁሉ የእኔ ነው።
9
አዲሱ ቤተ መቅደስ ከፊተኛው ይበልጥ የተዋበ ይሆናል፤ እኔም በዚያ ለሕዝቤ የተሟላ ሰላምን እሰጣለሁ፤” የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
10
ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ዘጠነኛው ወር በገባ በሃያ አራተኛው ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነቢዩ ሐጌ አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፤
11
“ካህናቱን ስለ ሕጉ ጠይቃቸው፤
12
ለምሳሌ አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ ከመሠዊያ ላይ ወስዶ በመጐናጸፊያው ጠቅልሎ ቢይዝ፥ ልብሱም እንጀራና ወጥ፥ የወይን ጠጅና ዘይት ወይም ማናቸውንም ዐይነት ምግብ ቢነካ፥ ምግቡ ሁሉ በዚያ ሰው ምክንያት የተቀደሰ ሊሆን ይችላልን?” በላቸው፤ በዚህ መሠረት ነቢዩ ከጠየቃቸው በኋላ፥ ካህናቱ “የተቀደሰ ሊሆን አይችልም” ሲሉ መለሱ።
13
ሐጌም እንደገና “ሬሳ በመዳሰስ የረከሰ አንድ ሰው፥ ከነዚህ የምግብ ዐይነቶች አንዱን ቢነካ፥ ያ የተነካው ምግብ በዕርግጥ ይረክሳልን?” ሲል ጠየቃቸው። ካህናቱም “አዎ፥ ይረክሳል” ሲሉ መለሱለት።
14
ሐጌም እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ በሙሉ እንደዚያው ነው፤ ስለዚህ ሥራቸውና የሚያቀርቡት ቊርባን የረከሰ ነው” ይላል እግዚአብሔር።
15
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ምን እንደ ደረሰባችሁ አታስተውሉምን? እነሆ፥ ቤተ መቅደሱን መልሳችሁ መሥራት ከመጀመራችሁ በፊት፥
16
ሁለት መቶ ኪሎ እህል ለማግኘት ወደ ምርት ማከማቻው ሄዳችሁ፤ ነገር ግን ያገኛችሁት እህል አንድ መቶ ኪሎ ብቻ ነበረ፤ አንድ መቶ ሊትር የወይን ጠጅ ለማግኘት ፈልጋችሁ ወደ ወይኑ መጭመቂያ ሄዳችሁ፤ ነገር ግን ያገኛችሁት የወይን ጠጅ አርባ ሊትር ብቻ ነበረ፤
17
እናንተንና የሥራችሁን ውጤት ሁሉ በዋግ፥ በሌላም በተክሎች በሽታና በበረዶ መታሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ግን በንስሓ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
18
እነሆ ዘጠነኛው ወር ከገባ ከዛሬ ከኻያ አራተኛው ቀን ጀምሮ አስተውሉ፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት ከተጣለበት ቀን ጀምሮ አስተውሉ።
19
አሁን ለዘር የሚሆን እህል በጐተራ ባይኖር የወይንና የበለስ፥ የሮማንና የወይራም ተክል ሁሉ ገና ፍሬ ባይሰጥም ከዚህ ቀን ጀምሮ እኔ በረከትን እሰጣችኋለሁ።”
20
በዚያው ወር በሃያ አራተኛው ቀን እግዚአብሔር እንደገና ለነቢዩ ለሐጌ ተናገረ።
21
የይሁዳ ገዢ ለሆነው ለዘሩባቤል እንዲህ ብለህ ተናገር፦ “ሰማይንና ምድርን የማናውጥበት ጊዜ ይመጣል፤
22
በዚያን ጊዜ፥ የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ ኀይላቸውንም እንዳልነበረ አደርጋለሁ፤ ሠረገላ ነጂዎችን ከነሠረገሎቻቸው እገለብጣለሁ፤ ፈረሶቻቸው ያልቃሉ፤ ፈረሰኞቻቸውም እርስ በርሳቸው ይጋደላሉ፤
23
አገልጋዬ ዘሩባቤል ሆይ! እኔ አንተን መርጬሃለሁ፤ አንድ ቀን መሪ እንድትሆን አንተን ለይቼ እንደ ማኅተም ቀለበቴ አደርግሃለሁ፤” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
All chapters:
1
2