bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Hebrews 3
Hebrews 3
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 4 →
1
ስለዚህ ለሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ የተቀደሳችሁ ምእመናን ሆይ! የእምነታችን ሐዋርያና የካህናት አለቃ ኢየሱስን አስቡ።
2
ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ታማኝ እንደ ነበረ ኢየሱስም ለሾመው ለእግዚአብሔር ታማኝ ነበር።
3
ቤትን የሚሠራ ከቤቱ ይልቅ የበለጠ ክብር እንዳለው ሁሉ ኢየሱስም ከሙሴ ይልቅ የበለጠ ክብር ይገባዋል።
4
በእርግጥ ለእያንዳንዱ ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉን ነገር የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው።
5
ወደፊት መባል ለሚገባው ነገር ምስክር እንዲሆን ሙሴ በመላው በእግዚአብሔር ቤት እንደ አገልጋይ ታማኝ ነበር።
6
ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ የሆነው እንደ ልጅ ሆኖ ነው፤ ቤቱም እኛ ነን፤ ቤቱ የምንሆነውም የምንተማመንበትን ነገርና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ ነው።
7
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ
8
በበረሓ በተፈታተናችሁኝ ጊዜ እንዳመፃችሁት ዐይነት ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ፤
9
እዚያ አባቶቻችሁ ተፈታተኑኝ፤ ተገዳደሩኝም፤ አርባ ዓመት ያደረግኹትንም አዩ” ይላል እግዚአብሔር።
10
“ስለዚህ ያንን ትውልድ ተቈጥቼ፥ ‘ልባቸው ዘወትር ይሳሳታል፤ መንገዴንም አላወቁም’ አልኩ።”
11
ደግሞም፥ “ ‘እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም!’ ብዬ በቊጣዬ ምዬአለሁ።”
12
ወዳጆቼ ሆይ፥ ከእናንተ መካከል ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያርቅ ክፉና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።
13
ይልቅስ ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ በየቀኑ ተመካከሩ።
14
በመጀመሪያ የነበረንን እምነታችንን እስከ መጨረሻ አጽንተን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ወራሾች እንሆናለን።
15
ይህም “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ በዚያ በዐመፃው ጊዜ እንዳደረጋችሁት ዐይነት ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ” ተብሎ እንደ ተነገረው ነው።
16
ለመሆኑ እነዚያ ድምፁን ከሰሙ በኋላ ያመፁ እነማን ነበሩ? እነርሱ ሙሴ እየመራቸው ከግብጽ የወጡት ሁሉ አልነበሩምን?
17
እግዚአብሔርን አርባ ዓመት ሙሉ ሲያስቈጡት የኖሩ እነማን ነበሩ? እነዚያ ኃጢአት የሠሩና ሬሳቸው በበረሓ ወድቆ የቀረው አይደሉምን?
18
ደግሞስ እነዚያን ያልታዘዙትን ካልሆነ በቀር “ወደ ዕረፍቴ አትገቡም” ብሎ የማለባቸው እነማን ነበሩ?
19
እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ባለማመናቸው ምክንያት መሆኑን እናያለን።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13