bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Jonah 2
Jonah 2
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 3 →
1
ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ እንዲህ ሲል ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤
2
“እግዚአብሔር ሆይ! ተጨንቄ ሳለሁ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም መለስክልኝ፤ ርዳታህን ለማግኘት ጥልቅ ከሆነው ከሙታን ዓለም ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ሰማኸኝ።
3
ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕር መሠረት ጣልከኝ፤ በዙሪያዬም ውሃ ከበበኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ በላዬ ላይ አለፉ።
4
እኔ ከፊትህ የጠፋሁ ነኝ፤ ይሁን እንጂ ቅዱስ መቅደስህን እንደገና አያለሁ።
5
ውሃ እስከ አንገቴ ድረስ አጠለቀኝ፤ ባሕርም ፈጽሞ አሰጠመኝ፤ በባሕር ውስጥም የበቀለው ሣር ቅጠል በራሴ ላይ ተጠመጠመብኝ።
6
ወደ ተራራዎች ሥር ወረድኩ፤ ከዚያ በታች ባለው ምድርም ውስጥ ለዘለዓለም ሊዘጋብኝ ነበር፤ አንተ ግን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እኔን ከጥልቁ ውሃ አውጥተህ ሕይወቴን ታድናለህ።
7
ሕይወቴ እየተዳከመ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔርን አስታወስኩ፤ ወደ አንተ ወደ አምላኬ ጸለይኩ፤ ጸሎቴም ወደ ቤተ መቅደስህ ወደ አንተ መጣ።
8
የሐሰት አማልክትን የተከተሉ ሁሉ፥ ለአንተ ያላቸውን ታማኝነት ትተዋል።
9
ደኅንነት ከእግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ ከምስጋና መዝሙር ጋር መሥዋዕትን ለአንተ አቀርባለሁ፤ የተሳልኩትንም እሰጣለሁ።”
10
ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ዓሣው ዮናስን በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4