bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Titus 1
Titus 1
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 2 →
1
የእግዚአብሔር አገልጋይና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው፥ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች ለማጠንከርና የሃይማኖትንም እምነት ሙሉ በሙሉ እንዲያውቁ ለማድረግ ከተሾመ ከጳውሎስ የተላከ፦
2
ይህም እምነት በዘለዓለም ሕይወት ተስፋ ላይ የተመሠረተ ነው፤ የማይዋሸው አምላክ ይህን ሕይወት ለመስጠት ከዘመናት በፊት ቃል ገባልን።
3
ዘመኑም በደረሰ ጊዜ በአዳኛችን በእግዚአብሔር ትእዛዝ እኔ እንዳበሥር በተሰጠኝ ዐደራ አማካይነት እግዚአብሔር ቃሉን ገለጠ።
4
የጋራችን በሆነው እምነት በእውነት ልጄ ለሆንከው ለቲቶ፥ ከእግዚአብሔር አብና ከአዳኛችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለአንተ ይሁን።
5
አንተን በቀርጤስ የተውኩበት ምክንያት ያልተስተካከለውን እንድታስተካክልና ባዘዝኩህም መሠረት የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን በየከተማው እንድትሾም ነው።
6
የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል የሆነ፥ ስድ በመሆንና ባለመታዘዝ ምክንያት የማይወቀሱ አማኞች ልጆች ያሉት ሰው መሆን ይገባዋል።
7
ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) የእግዚአብሔርን ሥራ በዐደራ የተቀበለ ስለ ሆነ የማይነቀፍ መሆን አለበት፤ እንዲሁም የማይኰራ፥ በቶሎ የማይቈጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ መሆን አለበት።
8
ይልቅስ እንግዳ ተቀባይ፥ መልካም የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ ትክክለኛ፥ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ፥ በመጠን የሚኖር ይሁን።
9
እውነተኛውን ትምህርት በማስተማር ለመምከርና ለተቃዋሚዎችም መልስ ለመስጠት እንዲችል በተማረው መሠረት በአስተማማኝ ቃል ይጽና።
10
ብዙ ሰዎች፥ ይልቁንም ከአይሁድ ወገን የሆኑ የግዝረትን ሥርዓት የሚከተሉ፥ የማይታዘዙ፥ በከንቱ የሚለፈልፉና የሚያታልሉ አሉ።
11
እነዚህን ሰዎች ዝም ማሰኘት ይገባል፤ እነርሱ በሚያሳፍር ትርፍ ለማግኘት የማይገባውን ነገር እያስተማሩ ቤተሰቦችን በሙሉ ያናውጣሉ።
12
ከእነርሱ አንዱ የሆነው የገዛ ራሳቸው ነቢይ “የቀርጤስ ሰዎች ሁልጊዜ ውሸታሞች፥ ክፉ አውሬዎች፥ ሥራ ፈት ሆዳሞች ናቸው” ብሎአል።
13
ይህም ምስክርነት እውነት ነው፤ ስለዚህ የተሟላ እምነት እንዲኖራቸው እነዚህን ሰዎች ገሥጻቸው።
14
የአይሁድን ተረት እንዳይከተሉና እውነትን የሚቃወሙትን ሰዎች ትእዛዝ እንዳይሰሙ በብርቱ ገሥጻቸው።
15
ለንጹሖች፥ ሁሉ ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሶችና ለማያምኑ ሰዎች ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሮአቸውም ሆነ ኅሊናቸው የረከሰ ነው።
16
“እግዚአብሔርን እናውቃለን” ይላሉ፤ በሥራቸው ግን ይክዱታል፤ እነርሱ አጸያፊዎች፥ የማይታዘዙና ምንም መልካም ሥራ ማድረግ የማይችሉ ናቸው።
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 2 →
All chapters:
1
2
3