bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
1 Samuel 3
1 Samuel 3
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 4 →
1
ብላቴናው ሳሙኤልም በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር።
2
በዚያም ዘመን እንዲህ ሆነ፤ ዔሊም በስፍራው ተኝቶ ሳለ፥ ዐይኖቹ መፍዘዝ ጀምረው ነበር። ማየትም አይችልም ነበር።
3
የእግዚአብሔርም መብራት ገና አልጠፋም ነበር፤ ሳሙኤልም የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር መቅደስ ተኝቶ ነበር፤
4
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “ሳሙኤል! ሳሙኤል” ብሎ ጠራው፤ እርሱም፥ “እነሆኝ” አለ።
5
ወደ ዔሊም ሮጠ፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለው። እርሱም፥ “አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው። ሄዶም ተኛ።
6
እግዚአብሔርም ደግሞ፥ “ሳሙኤል! ሳሙኤል” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሥቶ ዳግመኛ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለ። እርሱም፥ “አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ” አለው።
7
ሳሙኤል ግን ከዚህ በፊት ገና እግዚአብሔርን አላወቀም ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር።
8
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንደ ገና ሦስተኛ ጊዜ ጠራው። እርሱም ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለ። ዔሊም እግዚአብሔር ልጁን እንደ ጠራው አስተዋለ።
9
ዔሊም ሳሙኤልን፥ “ልጄ፥ ሄደህ ተኛ፤ ቢጠራህም፦ አቤቱ፥ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር በለው፥” አለው። ሳሙኤልም ሄዶ በስፍራው ተኛ።
10
እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፤ እንደ ቀድሞውም ጠራው። ሳሙኤልም፥ “ባሪያህ ይሰማልና ተናገር” አለ።
11
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፥ “እነሆ የሰማውን ሁሉ ሁለቱን ጆሮዎቹን ጭው የሚያደርግ ነገሬን በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ።
12
በዚያም ቀን በቤቱ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸናለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈጽምበታለሁ።
13
ልጆቹ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ እንዳደረጉ ዐውቆ አልገሠጻቸውምና ስለ ልጆቹ ኀጢአት ለዘለዓለም ቤቱን እንደምበቀል አስታውቄዋለሁ።
14
ስለዚህም የዔሊ ቤት ኀጢአት በዕጣንና በመሥዋዕት ለዘለዓለም እንዳይሰረይለት ለዔሊ ቤት ምያለሁ።”
15
ሳሙኤልም እስኪነጋ ተኛ፥ ማልዶም ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት ደጅ ከፈተ። ሳሙኤልም ራእዩን ለዔሊ መንገር ፈራ።
16
ዔሊም ሳሙኤልን ጠርቶ፥ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ” አለ።
17
እርሱም፥ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? ከእኔ አትሸሽግ፤ ከነገረህና ከሰማኸው ነገር ሁሉ የሸሸግኸኝ እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብህ፤ እንዲህም ይጨምርብህ” አለው።
18
ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፤ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።
19
ሳሙኤልም አደገ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ከቃሉም አንዳች በምድር ላይ አይወድቅም ነበር።
20
እስራኤልም ሁሉ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሳሙኤል ለእግዚአብሔር ነቢይ ይሆን ዘንድ የታመነ እንደ ሆነ ዐወቀ።
21
እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ። እግዚአብሔር ለሳሙኤል ይገለጥለት ነበርና። ሳሙኤልም ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ በእስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደ ሆነ ታመነ። ዔሊም እጅግ አረጀ፥ ልጆቹ ግን በክፋት ጸንተው ኖሩ፤ መንገዳቸውም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31