bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
1 Samuel 31
1 Samuel 31
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 30
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
1
ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ተዋግተውም በጌላቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።
2
ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን ተከትለው አገኙአቸው። ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን፥ ሜልኪሳንም ገደሉአቸው።
3
ሰልፍም በሳኦል ላይ ጠነከረ፤ ቀስተኞችም አገኙት፤ ታፋውንም ወጉት።
4
ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥ “እነዚህ ቈላፋን መጥተው እንዳይወጉኝና እንዳይሳለቁብኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ” አለ። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበርና እንቢ አለ። ሳኦልም ሰይፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።
5
ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል እንደ ሞተ ባየ ጊዜ እርሱ ደግሞ በሰይፉ ላይ ወደቀ። ከእርሱም ጋር ሞተ።
6
በዚያም ቀን ሳኦል ሦስቱም ልጆቹ ጋሻ ጃግሬውም በአንድ ላይ ሞቱ።
7
በሸለቆውም ማዶና በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያን የእስራኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቹን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።
8
በማግሥቱም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጌላቡሄ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።
9
አገላብጠውም የጦር መሣሪያዎችን ገፈፉ፤ በዙሪያቸውም ላሉ ለጣዖታቱና ለሕዝቡ የምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ሀገር ሁሉ ላኩ።
10
የጦር መሣሪያውንም በአስታሮት መቅደስ ውስጥ አኖሩት። ሬሳውንም በቤትሶም ቅጥር ላይ አንጠለጠሉት።
11
ፍልስጥኤማውያንም በሳኦል ላይ ያደረጉትን የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች በሰሙ ጊዜ፥ ጀግኖች ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ፥
12
የሳኦልንም ሬሳ፥ የልጁ የዮናታንንም ሬሳ ከቤትሶም ቅጥር ላይ አወረዱ፤ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በዚያም አቃጠሉአቸው።
13
አጥንቶቻቸውንም ወሰዱ፤ በኢያቢስም ባለው የእርሻ ቦታ ቀበሩአቸው፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።
← Chapter 30
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31