bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
/
Jonah 2
Jonah 2
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 3 →
1
ጌታም ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።
2
በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ዮናስ ወደ ጌታ ወደ አምላኩ ጸለየ።
3
እንዲህም አለ፦ “በመከራዬ ሆኜ ጌታን ጠራሁት፥ እርሱም መለሰልኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም ሰማህ።
4
ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ልብ ጣልኸኝ፥ ወንዝም ከበበኝ፥ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ ላይ አለፉ።
5
እኔም፦ ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ አልሁ ነገር ግን ቅዱስ መቅደስህን ዳግም አያለሁ።
6
ውኆች እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር ከበበኝ፥ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠመጠመ።
7
ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፥ የምድር መወርወሪያዎችዋ ለዘለዓለም ተዘጉብኝ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ አንተ ግን ሕይወቴን ከጉድጓድ አወጣሃት።
8
ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ ጌታን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ መጣች።
9
ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።
10
እኔ ግን ከምስጋና ቃል ጋር እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እፈፅማለሁ። ደኅንነት ከጌታ ነውና።”
11
ጌታም ዓሣውን ተናገረው፥ እርሱም ዮናስን በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4