bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
/
Jonah 3
Jonah 3
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 4 →
1
የጌታም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ዮናስ መጣ፥ እንዲህ አለው፦
2
“ተነሥ፥ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ እኔ የምነግርህን መልዕክት አውጅ።”
3
ዮናስም ተነሣና ጌታ እንደ ተናገረው ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች፥ ለማቋረጥም ሦስት ቀን ይፈጅ ነበር።
4
ዮናስ ወደ ከተማይቱ መግባት ጀመረ፥ የአንድ ቀን መንገድ ያህል እንደ ገባ “አሁንም ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች” ብሎ ጮኸ።
5
የነነዌም ሰዎች በእግዚአብሔር አመኑ፤ ጾምም አወጁ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።
6
ይህ ወሬ ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፥ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ፥ ማቅ ለበሶ በአመድም ላይ ተቀመጠ።
7
በነነዌ ሁሉ ይህንን አዋጅ አስነገረ፦ በንጉሡና በመኳንንቱ ትእዛዝ መሠረት፥ ሰውም ሆነ እንስሳ፥ ከብትም ሆነ በግ አንዳች አይቅመሱ፤ አይሰማሩ፥ ውኃም አይጠጡ፥
8
ሰውም ሆነ እንስሳ በማቅ ይሸፈኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎች ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በመዳፋቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።
9
እኛ እንዳንጠፋ፥ እግዚአብሔር ራርቶ ከሚነደው ቁጣው ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?
10
እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፥ እግዚአብሔርም ራርቶ አደርግባችኋለሁ ብሎ የተናገረውን ክፉ ነገር አላደረገውም።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4