bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
1 Chronicles 2
1 Chronicles 2
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 3 →
1
የእስራኤል ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣
2
ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ አሴር።
3
የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።
4
የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም በአጠቃላይ አምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።
5
የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ ኤስሮም፣ ሐሙል።
6
የዛራ ወንዶች ልጆች፤ ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ ፤ በአጠቃላይ አምስት ናቸው።
7
የከርሚ ወንድ ልጅ አካን ፤ እርሱም ፈጽሞ መደምሰስ የነበረበትን ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።
8
የኤታን ወንድ ልጅ፤ አዛርያ።
9
የኤስሮም ወንዶች ልጆች፤ ይረሕምኤል፣ አራም፣ ካሌብ።
10
አራም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤
11
ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ።
12
ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ።
13
የእሴይ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣ ሦስተኛ ልጁ ሣማ፣
14
አራተኛ ልጁ ናትናኤል፣ አምስተኛ ልጁ ራዳይ፣
15
ስድስተኛ ልጁ አሳም፣ ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።
16
እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣኤል ነበሩ።
17
አቢግያ አሜሳይን ወለደች፤ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።
18
የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ ከዓዙባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ያሳር፣ ሶባብ፣ አርዶን።
19
ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።
20
ሆር ኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
21
ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።
22
ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር።
23
ይሁን እንጂ ጌሹርና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ስድሳ መንደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት ። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ነበሩ።
24
ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።
25
የኤስሮም የበኵር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼም፣ አኪያ።
26
ይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናም እናት ነበረች።
27
የይረሕምኤል የበኵር ልጁ የራም ወንዶች፤ መዓስ፣ ያሚን፣ ዔቄር።
28
የኦናም ወንዶች ልጆች፤ ሸማይና ያዳ። የሸማይ ወንዶች ልጆች፤ ናዳብና አቢሱር።
29
የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።
30
የናባድ ወንዶች ልጆች፤ ሴሌድ፣ አፋይም፤ ሴሌድ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
31
የአፋይም ወንድ ልጅ፤ ይሽዒ። ይሽዒም ሶሳን ወለደ። ሶሳን አሕላይን ወለደ።
32
የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ዮናታን፤ ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
33
የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ ፌሌት፣ ዛዛ። እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።
34
ሶሳን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበረው።
35
ሶሳን ልጁን ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፤ እርሷም ዓታይ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት።
36
ዓታይ ናታንን ወለደ፤ ናታንም ዛባድን ወለደ፤
37
ዛባድ ኤፍላልን ወለደ፤ ኤፍላል ዖቤድን ወለደ፤
38
ዖቤድ ኢዩን ወለደ፤ ኢዩ ዓዛርያስን ወለደ፤
39
ዓዛርያስ ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስ ኤልዓሣን ወለደ፤
40
ኤልዓሣ ሲስማይን ወለደ፤ ሲስማይ ሰሎምን ወለደ፤
41
ሰሎም የቃምያን ወለደ፤ የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።
42
የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ሞሳ ሲሆን፣ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪሳም ኬብሮንን ወለደ።
43
የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ ቆሬ፣ ተፉዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ።
44
ሽማዕ ረሐምን ወለደ፤ ረሐምም ዮርቅዓምን ወለደ። ሬቄም ሸማይን ወለደ፤
45
ሸማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤት ጹርን ወለደ።
46
የካሌብ ቁባት ዔፉ ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች። ሐራንም ጋዜዝን ወለደ።
47
የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤ ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።
48
የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደችለት።
49
እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።
50
እነዚህ ሁሉ የካሌብ ዘሮች ነበሩ። የኤፍራታ የበኵር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች፤ ሦባል የቂርያትይዓሪም አባት፤
51
ሰልሞን የቤተ ልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።
52
የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤ የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤
53
እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ጐሣዎች፤ ይትራውያን፣ ፉታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፣ ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ከእነዚህ የመጡ ጐሣዎች ነበሩ።
54
የሰልሞን ዘሮች፤ ቤተ ልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኩሌታ፣ ጾርዓውያን።
55
በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጐሣዎች ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29