bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Chronicles 3
2 Chronicles 3
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 4 →
1
ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ዳዊት ባዘጋጀው ቦታ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ።
2
በነገሠም በአራተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በሁለተኛው ቀን ቤተ መቅደሱን መሥራት ጀመረ።
3
ሰሎሞን ለመቅደሱ ሕንጻ የጣለው መሠረት በቀድሞው ስፍር ልክ ርዝመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር።
4
በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ላይ ያለው በረንዳ ርዝመቱ በቤተ መቅደሱ ወርድ ልክ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ከፍታውም ሃያ ክንድ ነበር። ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።
5
የቤተ መቅደሱን ዋና ክፍል በጥድ ዕንጨት አልብሶ በተጣራ ወርቅ ለበጠው፤ የዘንባባና የሰንሰለት አምሳልም ቀረጸበት።
6
ቤተ መቅደሱን በከበረ ድንጋይ አስጌጠው፤ የተጠቀመበትም ወርቅ የፈርዋይም ወርቅ ነበር።
7
የጣራውን ተሸካሚዎች፣ መቃኖችን፣ የቤተ መቅደሱን ግድግዳና መዝጊያዎች በወርቅ ለበጠ፤ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቤልን ምስል ቀረጸ።
8
እንደዚሁም ቅድስተ ቅዱሳኑን ሠራ፤ ርዝመቱ ከቤተ መቅደሱ ወርድ ጋር እኩል ሲሆን፣ ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ስፋቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡንም በስድስት መቶ መክሊት የተጣራ ወርቅ ለበጠው።
9
የወርቅ ምስማሮቹም አምሳ ሰቅል ይመዝኑ ነበር፤ የላይኛውንም ክፍሎች እንደዚሁ በወርቅ ለበጠ።
10
በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሁለት ኪሩቤል ምስል አስቀርጾ በወርቅ ለበጣቸው።
11
ከዳር እስከ ዳር ገጥሞ የተዘረጋው የኪሩቤል ክንፍ በጠቅላላው ሃያ ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንዱ ክንፍ አምስት ክንድ ሆኖ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ሲነካ፣ ሌላው አምስት ክንድ የሆነው ክንፉ ደግሞ የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።
12
እንደዚሁም የሁለተኛው ኪሩብ አንዱ ክንፍ አምስት ክንድ ሆኖ በአንጻሩ ያለውን የቤተ መቅደስ ግድግዳ ሲነካ፣ አምስት ክንድ የሆነው ሌላው ክንፉ ደግሞ የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።
13
የተዘረጋው የእነዚህ ኪሩቤል ክንፍ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ፊታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል አዙረው በእግራቸው ቆመዋል።
14
ደግሞም ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከደማቅ ቀይ ፈትልና ከቀጭን በፍታ መጋረጃ ሠርቶ፣ የኪሩቤልን ምስል በጥልፍ ጠለፈበት።
15
በቤተ መቅደሱም ፊት ለፊት በአንድነት ቁመቱ ሠላሳ አምስት ክንድ የሆነ፣ በእያንዳንዱም ላይ አምስት ክንድ ጕልላት ያለው ሁለት ዐምድ ሠራ።
16
እርስ በርሳቸው የተጠላለፉ ሰንሰለቶች ሠርቶ ከዐምዶቹ ጫፍ ጋር አገናኛቸው፤ ከዚያም መቶ የሮማን ፍሬዎች ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋር አያያዛቸው።
17
ዐምዶቹንም አንዱን በደቡብ፣ ሌላውን በሰሜን አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በደቡብ በኩል ያለውን፣ “ያኪን”፣ በሰሜን በኩል ያለውንም፣ “ቦዔዝ” ብሎ ጠራቸው።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36