bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Chronicles 4
2 Chronicles 4
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 5 →
1
ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱ ዐሥር ክንድ የሆነ የናስ መሠዊያ ሠራ።
2
እንዲሁም የጐኑ ስፋት ከጠርዝ እስከ ጠርዝ ዐሥር ክንድ፣ ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ ክብ በርሜል ቀልጦ ከፈሰሰ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ ሆነ።
3
ከበርሜሉ ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኮርማ ቅርጾች ነበሩበት፤ ኮርማዎቹም ከበርሜሉ ጋር አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር።
4
በርሜሉ በዐሥራ ሁለት ኮርማዎች ላይ የቆመ ሲሆን፣ ኮርማዎቹም ሦስቱ ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር። በርሜሉ በእነዚህ ላይ ያረፈ ሲሆን፣ የሁሉም ጀርባ ወደ መካከል የዞረ ነበር።
5
የበርሜሉ ውፍረት አንድ ስንዝር፣ ከንፈሩ ደግሞ የጽዋ ከንፈር ወይም የሱፍ አበባ ይመስል ነበር፤ ይህም ሦስት ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ የሚይዝ ነበር።
6
እንዲሁም ዐሥር የመታጠቢያ ገንዳዎች አሠርቶ አምስቱን በደቡብ፣ አምስቱን ደግሞ በሰሜን በኩል አስቀመጠ፤ ገንዳዎቹ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡት ነገሮች የሚታጠቡባቸው ሲሆኑ፣ በርሜሉ ግን ለካህናት መታጠቢያ የሚያገለግል ነበር።
7
በተሰጠው የአሠራር መመሪያ መሠረት፣ ዐሥር የወርቅ መቅረዞች ሠርቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት፣ አምስቱን በስተ ደቡብ፣ አምስቱን በስተ ሰሜን አኖራቸው።
8
ዐሥር ጠረጴዛ ሠርቶም ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት አምስቱን በስተ ደቡብ፣ አምስቱን ደግሞ በስተ ሰሜን በኩል አኖራቸው፤ ደግሞም አንድ መቶ ጐድጓዳ የወርቅ ሳሕኖች ሠራ።
9
የካህናቱንም አደባባይ ሠራ፤ እንዲሁም ታላቁን አደባባይና በሮቹን ከሠራ በኋላ በናስ ለበጣቸው።
10
በርሜሉንም ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ ምሥራቅ ባለው ማእዘን በቀኝ በኩል አኖረው።
11
እንዲሁም ምንቸቱን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ። ኪራምም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ለንጉሥ ሰሎሞን ሠርቶ ጨረሰ፤ እነዚህም፦
12
ሁለቱ ዐምዶች፣ በአዕማዱ ጫፍ ላይ ያሉት ሁለት ባለ ሳሕን ቅርጽ ጕልላት በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለቱን፣ ባለ ሳሕን ቅርጽ ጕልላት የሚያስጌጡ ሁለት ዙር መርበቦች፤
13
በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለቱን፣ ባለ ሳሕን ቅርጽ ጕልላት እንዲያስጌጡ ለእያንዳንዱ መርበብ ሁለት ዙር ሮማኖች ለሁለቱም ዙር መርበቦች በድምሩ አራት መቶ ሮማኖች፤
14
መቆሚያዎች ከነመታጠቢያ ሳሕኖቻቸው፤
15
በርሜሉና እርሱን የተሸከሙት ዐሥራ ሁለት ኮርማዎች፤
16
ምንቸቶችና መጫሪያዎች፣ ሜንጦዎችና ከነዚሁም ጋር የተያያዙ ዕቃዎች። ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆን ለሰሎሞን የሠራቸው ዕቃዎች በሙሉ ከተወለወለ ናስ የተሠሩ ነበሩ።
17
ንጉሡም እነዚህ ዕቃዎች በዮርዳኖስ ሸለቆ፣ በሱኮትና በጽሬዳ መካከል ባለው በሸክላ ዐፈር ቦታ ቀልጠው በሸክላ ቅርጽ ተሠርተው እንዲወጡ አደረገ።
18
እነዚህ ሰሎሞን ያሠራቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ ብዙዎች ስለሆኑ የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ሆነ አልታወቀም ነበር።
19
እንደዚሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሠራ፤ እነዚህም፦ የወርቅ መሠዊያ፣ የገጸ ኅብስቱ ጠረጴዛ፣
20
በተሰጠው መመሪያ መሠረት፣ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት እንዲነድዱ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞች ከነቀንዲሎቻቸው፣
21
የወርቅ አበባ ቅርጽ ሥራዎች፣ ቀንዲሎችና መኰስተሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።
22
ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ የመብራት ማጥፊያዎች፣ ለመርጨት የሚያገለግሉ ጐድጓዳ ሳሕኖች፣ ጭልፋዎችና ጥናዎች፣ እንደዚሁም የቤተ መቅደሱ የወርቅ መዝጊያዎች፣ ይኸውም የቅድስተ ቅዱሳኑ የውስጠኛው መዝጊያዎችና የቤተ መቅደሱ ዋናው አዳራሽ መዝጊያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 5 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36