bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Isaiah 22
Isaiah 22
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 21
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 51
Chapter 52
Chapter 53
Chapter 54
Chapter 55
Chapter 56
Chapter 57
Chapter 58
Chapter 59
Chapter 60
Chapter 61
Chapter 62
Chapter 63
Chapter 64
Chapter 65
Chapter 66
Chapter 23 →
1
ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ንግር፤ እስቲ ምን ቢጨንቃችሁ ነው ሁላችሁም ሰገነት ላይ የወጣችሁት?
2
አንቺ ጫጫታ የሞላብሽ ከተማ፤ የውካታና የፈንጠዝያ ከተማ ሆይ፤ የተገደሉብሽ በሰይፍ የተሠዉ አይደሉም፤ በጦርነትም አልሞቱም።
3
መሪዎችሽ በሙሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል፤ ቀስት እንኳ ሳያነሡ ተማርከዋል፤ ጠላት ገና በሩቅ ሳለ የሸሻችሁ ሁሉ፣ ተይዛችሁ በአንድነት ታስራችኋል።
4
ስለዚህ፣ “ከእኔ ራቁ፤ አምርሬ ላልቅስበት፣ ስለ ሕዝቤ ጥፋት፣ ልታጽናኑኝ አትሞክሩ” አልሁ።
5
ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በራእይ ሸለቆ፣ የመጯጯኺያ፣ የመረገጥና የሽብር፣ ቅጥሮችን የማፈራረስ፣ ወደ ተራሮችም የሚጮኽበት ቀን አለው።
6
ኤላም የፍላጻ ሰገባ፣ ፈረሷንና ሠረገላዋን አዘጋጀች፤ ቂርም ጋሻዋን አነገበች።
7
መልካሞቹ ሸለቆዎችሽ በሠረገሎች ተሞልተዋል፤ ፈረሰኞችም በከተማዪቱ በሮች ላይ ቆመዋል፤
8
የይሁዳን መከላከያዎች ገልጧል። በዚያን ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን፣ የጦር መሣሪያ ተመለከትህ፤
9
የዳዊት ከተማ ብዙ ፍርስራሾች እንዳሉበት አያችሁ፤ በታችኛውም ኵሬ፣ ውሃ አጠራቀማችሁ።
10
በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤ ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ።
11
ለጥንቱ ኵሬ ውሃ የሚሆን፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል ውሃ ማጠራቀሚያ ሠራችሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገውን አልተመለከታችሁም፤ ቀድሞ ዐቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።
12
በዚያን ቀን ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ፣ እንድታለቅሱና በዋይታ እንድትጮኹ፣ ጠጕራችሁን እንድትነጩ ማቅም እንድትለብሱ ጠራችሁ።
13
ነገር ግን እነሆ፤ ተድላና ደስታ፣ ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ፤ “እንብላ እንጠጣ፣ ነገ እንሞታለንና” አላችሁ።
14
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ገለጠልኝ፤ እንዲህም ሲል በጆሮዬ ሰማሁ፤ “ይህ ኀጢአት እስከምትሞቱበት ቀን ድረስ አይሰረይላችሁም” ይላል ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ።
15
ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሂድና ይህን መጋቢ፣ የቤቱንም ኀላፊ ሳምናስን እንዲህ በለው፤
16
‘እዚህ ምን ታደርጋለህ? በዚህ ስፍራ ለራስህ መቃብርን እንድታዘጋጅ፣ በከፍታውም ላይ መቀበሪያህን እንድትወቅር፣ ሬሳህ የሚያርፍበትንም ዐለት እንድትጠርብ ማን ፈቀደልህ?’
17
“አንተ ኀያል ሰው ሆይ፤ ተጠንቀቅ፤ እግዚአብሔር አጥብቆ ሊይዝህ፣ በእጆቹም ጨብጦ ሊወረውርህ ነው።
18
አዙሮ አዙሮ እንደ ሩር አጡዞ፣ ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል፤ አንተ የጌታህ ቤት ዕፍረት! በዚያ ትሞታለህ፤ የክብር ሠረገሎችህም እዚያ ይቀራሉ።
19
ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ ከኀላፊነትህም ትባረራለህ።
20
“በዚያን ቀን አገልጋዬን፣ የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፤
21
መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህን አስታጥቀዋለሁ፤ ሥልጣንህንም አስረክበዋለሁ። እርሱም በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፣ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።
22
የዳዊትን ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም።
23
በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ካስማ እተክለዋለሁ፤ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል።
24
የቤተ ሰቡ ክብር፣ ልጅና የልጅ ልጅ፣ እንዲሁም ከማሰሮ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በእርሱ ላይ ይንጠለጠላል።
25
“በዚያ ቀን” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ፣ “በአስተማማኝ ስፍራ የተተከለ ካስማ ይነቀላል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፤ በእርሱም ላይ የተንጠለጠለው ሸክም ወድቆ ይከሰከሳል፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሯልና።
← Chapter 21
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 51
Chapter 52
Chapter 53
Chapter 54
Chapter 55
Chapter 56
Chapter 57
Chapter 58
Chapter 59
Chapter 60
Chapter 61
Chapter 62
Chapter 63
Chapter 64
Chapter 65
Chapter 66
Chapter 23 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66