bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Isaiah 45
Isaiah 45
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 44
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 51
Chapter 52
Chapter 53
Chapter 54
Chapter 55
Chapter 56
Chapter 57
Chapter 58
Chapter 59
Chapter 60
Chapter 61
Chapter 62
Chapter 63
Chapter 64
Chapter 65
Chapter 66
Chapter 46 →
1
“ለቀባሁት፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት፣ ነገሥታትን ትጥቅ አስፈታ ዘንድ፣ ሕዝብን ሁሉ ላስገዛለት፣ ደጆች እንዳይዘጉ፣ በሮቹን በፊቱ ለምከፍትለት፣ ለቂሮስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
2
‘በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራሮችን እደለድላለሁ፤ የናስ በሮችን እሰብራለሁ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም እቈርጣለሁ።
3
በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ፣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቅ ዘንድ፣ በተሰወረ ስፍራ የተከማቸውን ሀብት፣ በጨለማም ያለውን ንብረት እሰጥሃለሁ።
4
ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ መረጥሁት ስለ እስራኤል፣ አንተ ባታውቀኝ እንኳ፣ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ የክብርም ስም ሰጥቼሃለሁ።
5
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔ በቀር አምላክ የለም። አንተ ባታውቀኝም እንኳ፣ እኔ አበረታሃለሁ።
6
ይኸውም ሰዎች ከፀሓይ መውጫ፣ እስከ መጥለቂያው፣ ከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም።
7
እኔ ብርሃንን ሠራሁ፤ ጨለማንም ፈጠርሁ፤ አበለጽጋለሁ፤ አደኸያለሁ፤ ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’
8
“እናንት ሰማያት፣ ጽድቅን ከላይ አዝንቡ፤ ደመናትም ወደ ታች አንጠብጥቡ፤ ምድር ትከፈት፤ ድነት ይብቀል፤ ጽድቅም አብሮት ይደግ፤ እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።
9
“ከዐፈር ሸክላዎች መካከል፣ ከሠሪው ጋር ክርክር ለሚገጥም ወዮለት፤ ጭቃ፣ ሸክላ ሠሪውን፣ ‘ምን እየሠራህ ነው?’ ይለዋልን? የምትሠራውስ ሥራ፣ ‘እጅ የለህም’ ይልሃልን?
10
አባቱን፣ ‘የወለድኸው ምንድን ነው?’ ለሚል፣ እናቱንም፣ ‘ምን ወለድሽ’? ለሚል ወዮለት።
11
“የእስራኤል ቅዱስ፣ ሠሪውም የሆነ እግዚአብሔር ፣ ስለሚመጡ ነገሮች እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ ልጆቼ ትጠይቁኛላችሁን? ስለ እጆቼስ ሥራ ታዝዙኛላችሁን?
12
ምድርን የሠራሁ እኔ ነኝ፤ ሰውንም በላይዋ ፈጥሬአለሁ፤ እጆቼ ሰማያትን ዘርግተዋል፤ የሰማይንም ሰራዊት አሰማርቻለሁ።
13
ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቻለሁ፤ መንገዱን ሁሉ አስተካክዬለታለሁ፤ ከተማዬን እንደ ገና ይሠራታል፤ ምርኮኞቼን ያለ ክፍያ ወይም ያለ ዋጋ፣ ነጻ ያወጣል፤’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ።”
14
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የግብፅ ሀብትና የኢትዮጵያ ንግድ፣ ቁመተ ረዣዥሞቹ የሳባ ሰዎች፣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ የአንተ ይሆናሉ፤ ከኋላ ይከተሉሃል፤ በሰንሰለትም ታስረው ወደ አንተ በመምጣት፣ በፊትህ እየሰገዱ፣ ‘በእውነት እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ብለው ይለምኑሃል።”
15
አዳኙ የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ አንተ በእውነት ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።
16
ጣዖት ሠሪዎች ሁሉ ያፍራሉ፤ ይቀልላሉ፤ በአንድነት ይዋረዳሉ።
17
እስራኤል ግን በእግዚአብሔር ፣ በዘላለም ድነት ይድናል፤ እናንተም ለዘላለም፣ አታፍሩም፤ አትዋረዱም።
18
ሰማያትን የፈጠረ፣ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያበጃት፣ የሠራት፣ የመሠረታት፣ የሰው መኖሪያ እንጂ፣ ባዶ እንድትሆን ያልፈጠራት፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።
19
በጨለማ ምድር፣ በምስጢር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብም ዘር፣ ‘በከንቱ ፈልጉኝ’ አላልሁም። እኔ እግዚአብሔር እውነትን እናገራለሁ፤ ትክክለኛውንም ነገር ዐውጃለሁ።
20
“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንት ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።
21
ጕዳያችሁን ተናገሩ፤ አቅርቡ፤ ተሰብስበውም ይማከሩ። ይህን አስቀድሞ ማን ዐወጀ? ከጥንትስ ማን ተናገረ? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ጻድቅና አዳኝ የሆነ አምላክ፣ ከእኔ በቀር ማንም የለም፤ ከእኔ ሌላ አምላክ የለም።
22
“እናንት የምድር ዳርቻ ሁሉ፣ እኔ አምላክ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና፤ ትድኑ ዘንድ ወደ እኔ ተመለሱ።
23
ጕልበት ሁሉ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ አንደበትም ሁሉ በእኔ ይምላል፤ ብዬ በራሴ ምያለሁ፤ የማይታጠፍ ቃል፣ ከአፌ በጽድቅ ወጥቷል።
24
ስለ እኔም ሲናገሩ፣ ‘ጽድቅና ኀይል፣ በእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ይላሉ።” በእርሱ ላይ በቍጣ የተነሡ ሁሉ፣ ወደ እርሱ መጥተው ያፍራሉ።
25
ነገር ግን የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ ሞገስንም ያገኛሉ።
← Chapter 44
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 51
Chapter 52
Chapter 53
Chapter 54
Chapter 55
Chapter 56
Chapter 57
Chapter 58
Chapter 59
Chapter 60
Chapter 61
Chapter 62
Chapter 63
Chapter 64
Chapter 65
Chapter 66
Chapter 46 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66