bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Lamentations 1
Lamentations 1
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 2 →
1
በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ፣ እንዴት የተተወች ሆና ቀረች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው፣ እርሷ እንዴት እንደ መበለት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፣ አሁን ባሪያ ሆናለች።
2
በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጕንጮቿ ላይ ይወርዳል፤ ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል፣ የሚያጽናናት ማንም የለም፤ ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ ጠላቶቿም ሆነዋል።
3
በመከራና በመረገጥ ብዛት ይሁዳ ተማርካ ሄደች፤ በሕዝቦችም መካከል ተቀመጠች፤ የምታርፍበትንም ስፍራ ዐጣች፤ በጭንቀቷ መካከል ሳለች፣ አሳዳጆቿ ሁሉ አገኟት።
4
የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ፤ በዓላቷን ለማክበር የሚመጣ የለምና፤ በበሮቿ ሁሉ የሚገባና የሚወጣ የለም፤ ካህናቷ ይቃትታሉ፤ ደናግሏ ክፉኛ ዐዝነዋል፤ እርሷም በምሬት ትሠቃያለች።
5
ባላጋሮቿ ገዦቿ ሆኑ፤ ጠላቶቿ ተመችቷቸዋል፤ ከኀጢአቷ ብዛት የተነሣ፣ እግዚአብሔር ከባድ ሐዘን አምጥቶባታል። ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው፣ ወደ ግዞት ሄደዋል።
6
የጽዮን ሴት ልጅ፣ ግርማ ሞገሷ ሁሉ ተለይቷታል፤ መሳፍንቷ፣ መሰማሪያ እንዳጣ ዋሊያ ናቸው፤ በአሳዳጆቻቸው ፊት፣ በድካም ሸሹ።
7
በተጨነቀችባቸውና በተንከራተተችባቸው ቀናት፣ ኢየሩሳሌም በጥንት ዘመን የነበራትን፣ ሀብት ሁሉ ታስባለች፤ ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፣ የረዳት ማንም አልነበረም፤ ጠላቶቿ ተመለከቷት፤ በመፈራረሷም ሣቁ።
8
ኢየሩሳሌም ከባድ ኀጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህም የረከሰች ሆናለች፤ ያከበሯት ሁሉ ናቋት፤ ዕራቍቷን ሆና አይተዋታልና፤ እርሷ ራሷ ታጕረመርማለች፤ ወደ ኋላዋም ዘወር ብላለች።
9
ርኩሰቷ በቀሚሷ ላይ ታየ፤ ወደ ፊት የሚሆንባትን አላሰበችም፤ አወዳደቋ አስደንጋጭ ሆነ፤ የሚያጽናናትም አልነበረም፤ “ እግዚአብሔር ሆይ፤ መከራዬን ተመልከት፤ ጠላት ድል አድርጓልና!”
10
ዮድ በሀብቷ ሁሉ ላይ፣ ጠላት እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ የከለከልሃቸው፣ ጣዖት የሚያመልኩ አሕዛብ፣ ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።
11
እንጀራ በመፈለግ፣ ሕዝቧ ሁሉ በሥቃይ ይጮኻል፤ በሕይወት ለመኖር፣ የከበረ ሀብታቸውን በምግብ ይለውጣሉ፤ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ ተመልከተኝም፤ እኔ ተዋርጃለሁና።”
12
“እናንት መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ፤ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? ተመልከቱ፤ እዩም፤ በጽኑ ቍጣው ቀን፣ እግዚአብሔር ያመጣብኝን፣ በእኔ ላይ የደረሰውን፣ የእኔን መከራ የመሰለ መከራ አለን?
13
“ከከፍታ ስፍራ እሳትን ላከ፤ ወደ ታች ወደ ዐጥንቶቼም ሰደደው፤ በእግሮቼ ላይ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም ጣለኝ፤ ቀኑን ሙሉ በማድከም፣ ባዶ አድርጎ አስቀመጠኝ።
14
“ኀጢአቶቼ ቀንበር ሆኑ፤ በእጆቹ አንድ ላይ ተገመዱ፤ በዐንገቴም ላይ ተጭነዋል፤ ኀይሌንም አዳከመ፤ ልቋቋማቸው ለማልችላቸው፣ እርሱ አሳልፎ ሰጠኝ።
15
“በውስጤ ያሉትን ተዋጊዎች ሁሉ፣ እግዚአብሔር ተቃወመ፤ ጕልማሶቼን ለማድቀቅ፣ ሰራዊት በላዬ ላይ ጠራ ፤ ድንግሊቱን የይሁዳ ሴት ልጅ፣ እግዚአብሔር በወይን መጭመቂያ ውስጥ ረገጣት።
16
“የማለቅሰው ስለ እነዚህ ነገሮች ነው፤ ዐይኖቼ በእንባ ተሞልተዋል፣ ሊያጽናናኝ የቀረበ፣ መንፈሴንም ሊያረጋጋ የሞከረ ማንም የለም፤ ጠላት በርትቷልና ልጆቼ ተጨንቀዋል።”
17
ጽዮን እጆቿን ዘረጋች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ ጎረቤቶቹ ጠላቶቹ እንዲሆኑ፣ እግዚአብሔር በያዕቆብ ላይ ትእዛዝ አውጥቷል፤ ኢየሩሳሌምም በመካከላቸው፣ እንደ ርኩስ ነገር ተቈጠረች።
18
“ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔ ግን በትእዛዙ ላይ ዐመፅ አድርጌ ነበር፤ እናንተ ሕዝቦች ሁሉ ስሙ፤ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ወይዛዝርቶቼና ጐበዛዝቶቼ፣ ተማርከው ሄደዋል።
19
“ወዳጆቼን ጠራኋቸው፤ እነርሱ ግን ከዱኝ፤ ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ፣ ሕይወታቸውን ለማትረፍ፣ ምግብ ሲፈልጉ፣ በከተማዪቱ ውስጥ ዐለቁ።
20
“አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት ተጨንቄአለሁ! በውስጤ ተሠቃይቼአለሁ፤ በልቤ ታውኬአለሁ፤ እጅግ ዐመፀኛ ሆኛለሁና፤ በውጭ ሰይፍ ይፈጃል፤ በቤትም ውስጥ ሞት አለ።
21
“ሰዎች የሥቃይ ልቅሶዬን ሰሙ፤ የሚያጽናናኝ ግን ማንም የለም፤ ጠላቶቼ ሁሉ ጭንቀቴን ሰሙ፤ አንተ ባደረግኸውም ደስ አላቸው፤ አቤቱ የተናገርሃት ቀን ትምጣ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሁኑ።
22
“ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ ከኀጢአቴ ሁሉ የተነሣ፣ በእኔ ላይ እንዳደረግህብኝ፣ በእነርሱም ላይ አድርግባቸው፤ የሥቃይ ልቅሶዬ በዝቷል፤ ልቤም ደክሟል።”
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 2 →
All chapters:
1
2
3
4
5