bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Zephaniah 1
Zephaniah 1
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 2 →
1
በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤
2
“ማንኛውንም ነገር፣ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ” ይላል እግዚአብሔር ።
3
“ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ የሰማይን ወፎች፣ የባሕርንም ዓሦች አጠፋለሁ፤ ሰውን ከምድር ገጽ በማስወግድበት ጊዜ፣ ክፉዎች የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ” ይላል እግዚአብሔር ።
4
“እጄን በይሁዳ፣ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አነሣለሁ፤ የበኣልን ትሩፍ፣ የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ሁሉ ከዚህ ስፍራ አጠፋለሁ፤
5
የሰማይን ሰራዊት ለማምለክ፣ በሰገነት ላይ ወጥተው የሚሰግዱትን፣ ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፣ በስሙም እየማሉ፣ በሚልኮምም ደግሞ የሚምሉትን፣
6
እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ የሚመለሱትን፣ እግዚአብሔርን የማይፈልጉትን፣ እንዲረዳቸውም የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።”
7
በጌታ እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውንም ቀድሷል።
8
በእግዚአብሔር የመሥዋዕት ቀን፣ መሳፍንቱንና የንጉሡን ልጆች፣ እንግዳ ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ።
9
በዚያን ቀን፣ በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን ሁሉ፣ የአማልክታቸውን ቤት፣ በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።
10
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ቀን ‘ከዓሣ በር’ ጩኸት በሁለተኛው አደባባይ ዋይታ፣ ከኰረብቶችም ታላቅ ሽብር ይሰማል።
11
እናንት በመክቴሽ ገበያ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ።
12
በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ተንደላቅቀው የሚኖሩትን፣ በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣ ‘ክፉም ይሁን መልካም፣ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።
13
ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤታቸው ይፈራርሳል፤ ቤቶች ይሠራሉ፤ ነገር ግን አይኖሩባቸውም፤ ወይን ይተክላሉ፤ ጠጁን ግን አይጠጡም።”
14
“ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ ቅርብ ነው ፈጥኖም ይመጣል፤ በእግዚአብሔር ቀን የሚሰማው ልቅሶ መራራ ነው፤ በዚያ ጦረኛውም ምርር ብሎ ይጮኻል፤
15
ያ ቀን የመዓት ቀን፣ የመከራና የጭንቀት ቀን፣ የሁከትና የጥፋት ቀን፣ የጨለማና የጭጋግ ቀን፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤
16
ያ ቀን በተመሸጉ ከተሞችና፣ በረዣዥም ግንቦች ላይ፣ የመለከት ድምፅና የጦርነት ጩኸት የሚሰማበት ቀን ይሆናል።
17
“እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣ በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና። ደማቸው እንደ ትቢያ፣ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይጣላል።
18
በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም።” መላዪቱ ምድር፣ በቅናቱ ትበላለች፤ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣ ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና።
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 2 →
All chapters:
1
2
3