bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Zephaniah 2
Zephaniah 2
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 3 →
1
እናንት ዕረፍት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፤ በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ተከማቹም፤
2
የተወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣ ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣ የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣ፣ የእግዚአብሔር የመዓት ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ።
3
እናንት የምድር ትሑታን ሁሉ፣ ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤ ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤ በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ትሰወሩ ይሆናል።
4
ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤ አስቀሎናም ፈራርሳ ትቀራለች፤ አዛጦን በቀትር ባዶ ትሆናለች፤ አቃሮንም ትነቀላለች።
5
እናንት በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፣ የከሊታውያን ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁ! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፤ በአንቺ ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ “ፍጹም አጠፋሻለሁ፤ ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም።”
6
የቀርጤስ ሰዎች የሚኖሩበት በባሕሩ ዳር ያለው ምድር፣ የእረኞች መኖሪያና የበጎች በረት ይሆናል፤
7
ይህም ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሰጣል፤ እነርሱም በዚያ መሰማሪያ ያገኛሉ። በአስቀሎና ቤቶች ውስጥም በምሽት ይተኛሉ፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ ምርኳቸውንም ይመልስላቸዋል።
8
“የሞዓብን ስድብ፣ የአሞናውያንንም ፌዝ ሰምቻለሁ፤ ሕዝቤን ሰድበዋል፤ በምድራቸውም ላይ ዝተዋል።”
9
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ሞዓብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጕድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ። ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ።”
10
ከትዕቢታቸው የተነሣ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሰድበው ዘብተውበታልና፣
11
እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክት ሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣ እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።
12
“ኢትዮጵያውያን ሆይ፤ እናንተም፣ በሰይፌ ትገደላላችሁ።”
13
እጁን በሰሜን ላይ ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ ነነዌን ፍጹም ባድማ፣ እንደ ምድረ በዳም ደረቅ ያደርጋታል።
14
የበግና የከብት መንጋዎች፣ የፍጥረት ዐይነት ሁሉ በውስጧ ይመሰጋሉ፤ ጕጕትና ጃርት፣ በግንቦቿ ላይ ያድራሉ። ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ ፍርስራሽ በየደጃፉ ይከመራል፤ ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይገለጣሉ።
15
ተዘልላ የኖረች፣ ደስተኛዪቱ ከተማ ይህች ናት፤ እርሷም በልቧ፣ “እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ማንም የለም” ያለች፣ ታዲያ እንዴት የዱር አራዊት የሚመሰጉባት፣ ባድማ ሆና ቀረች? በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ፣ ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3