bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
2 Thessalonians 2
2 Thessalonians 2
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 3 →
1
ወንድሞች ሆይ! ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና እኛም ከእርሱ ጋር ለመሆን ስለ መሰብሰባችን ጉዳይ የምንለምናችሁ ይህን ነው፤
2
በትንቢት ወይም በቃል እንደ ተነገረ ወይም ከእኛ በመልእክት እንደ ተጻፈ አድርጋችሁ “የጌታ ቀን ደርሶአል” በማለት በቶሎ አእምሮአችሁ አይናወጥ፤ አትታወኩም፤
3
ማንም ሰው በምንም ዐይነት አያታላችሁ፤ አስቀድሞ ክሕደት ሳይመጣ፥ ገሃነም የሚገባው የዐመፅ ሰው የሆነውም ሳይገለጥ፥ ያ ቀን አይመጣም።
4
ይህ የዐመፅ ሰው አማልክት ተብለው ከሚመለኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ያደርጋል፤ “እግዚአብሔር ነኝ” እያለም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንኳ ለመቀመጥ ይደፍራል።
5
ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ይህን ነገር ነግሬአችሁ እንደ ነበረ አታስታውሱምን?
6
በተወሰነለት ጊዜ እስኪገለጥ ድረስ አሁን እንዳይገለጥ የሚከለክለው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።
7
ምሥጢራዊው የዐመፅ ኀይል አሁንም በመሥራት ላይ ነው፤ ሆኖም አሁን የሚከለከለው አለ፤ ይህም የሚሆነው ያ የሚከለክለው እስኪወገድ ድረስ ነው።
8
ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚያጠፋውና በግርማ መምጣቱ የሚደመስሰው የዐመፅ ሰው ይገለጣል።
9
የዐመፅ ሰው የሚመጣው በሰይጣን ኀይል አሳሳች ተአምራትንና ምልክቶችን አስደናቂ ነገሮችንም በማድረግ ነው፤
10
እንዲሁም የሚጠፉትን ሰዎች የሚያታልሉት ማናቸውንም ክፉ ነገሮችን በማድረግ ነው። እነዚህ ሰዎች የሚጠፉትም ለመዳን የሚያበቃቸውን እውነት ወደው ስላልተቀበሉ ነው።
11
በዚህ ምክንያት በሐሰት እንዲያምኑ እግዚአብሔር የሚያሳስት ኀይልን ይልክባቸዋል።
12
ይህም የሚሆነው እውነትን አናምንም ብለው በኃጢአት የሚደሰቱ ሁሉ እንዲፈረድባቸው ነው።
13
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማመስገን ይገባናል፤ የምናመሰግነውም እናንተ በመንፈስ ቅዱስ በመቀደሳችሁና እውነትን በማመናችሁ እንድትድኑ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለ መረጣችሁ ነው።
14
እግዚአብሔር እኛ ባበሠርናችሁ ወንጌል አማካይነት ለዚህ የጠራችሁ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር እንድትካፈሉ ነው።
15
ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ሆነ በመልእክታችን ከእኛ የተላለፈላችሁን ትምህርት አጥብቃችሁ ያዙ።
16
ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን፥ በጸጋውም የዘለዓለም መጽናናትን፥ መልካም ተስፋንም የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን
17
መልካም የሆነውን ሁሉ እንድታደርጉና እንድትናገሩ ልባችሁን ያጽናናው፤ መልካሙን ነገር ሁሉ እንድታደርጉና እንድትናገሩ ያበርታችሁ።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3