bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
2 Thessalonians 3
2 Thessalonians 3
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
1
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ዘንድ እንደሆነው ሁሉ የጌታ ቃል በፍጥነት እንዲስፋፋና እንዲከበር ለእኛ ጸልዩልን፤
2
እንዲሁም ቃሉን የሰሙት ሁሉ የሚያምኑ አይደሉም፤ ስለዚህ ከጠማሞችና ከክፉ ሰዎች እንድንድን ጸልዩልን።
3
ጌታ ግን ታማኝ ነው፤ እርሱ ያበረታችኋል፤ ከሰይጣንም ይጠብቃችኋል፤
4
የምናዛችሁን አሁንም ሆነ ወደፊት እንደምትፈጽሙት በጌታ እንተማመንባችኋለን።
5
ጌታ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ወደ ክርስቶስ ትዕግሥት ይምራው።
6
ወንድሞች ሆይ! ሥራ ፈት ከሆነውና ከእኛ በተላለፈላችሁ ትውፊት መሠረት ከማይኖር ክርስቲያን ሁሉ እንድትለዩ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።
7
የእኛን ምሳሌነት መከተል እንደሚገባችሁ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ እኛ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ ሥራ ፈቶች አልነበርንም፤
8
የማንንም እንጀራ በብላሽ አልበላንም፤ ይልቅስ ከእናንተ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆንበት በማለት ሌሊትና ቀን በመድከምና በመልፋት እንሠራ ነበር።
9
እንዲህም ያደረግነው እናንተ የእኛን ምሳሌነት እንድትከተሉ ብለን ነው እንጂ ከእናንተ ርዳታ ለማግኘት መብት ሳይኖረን ቀርቶ አይደለም።
10
ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ሊሠራ የማይፈልግ አይብላ” የሚል ደንብ ሰጥተናችሁ ነበር።
11
ይህን ያልንበት ምክንያት በመካከላችሁ አንዳንድ ሥራ ፈቶች እንዳሉ በመስማታችን ነው፤ እነዚህ ሰዎች በማያገባቸው ነገር እየገቡ ሌሎችን ከማወክ በቀር ምንም አይሠሩም።
12
እንደእነዚህ ያሉ ሰዎች ተረጋግተው እንዲሠሩና መተዳደሪያቸውን እንዲያገኙ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም።
13
እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! ደከምን ብላችሁ መልካም ከመሥራት አትቦዝኑ።
14
በዚህ መልእክት ያስተላለፍንላችሁን ምክር የማይቀበል ሰው ቢኖር እንዲህ ያለውን ሰው ልብ በሉት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አታድርጉ።
15
ሆኖም እንደ ወንድም ምከሩት እንጂ እንደ ጠላት አትቊጠሩት።
16
የሰላም ጌታ ራሱ ሁልጊዜ በሁሉም ነገር ሰላምን ይስጣችሁ፤ ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
17
ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍኩት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ በእኔ መልእክት ሁሉ የሚገኘው ምልክት ይህ ነው። የምጽፈውም እንዲህ ነው።
18
የጌታችን የኢየሱስ ክርሰቶስ ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
All chapters:
1
2
3